ኢትዮጵያዊው ተጫዋች ከኦማን ጂንዳል ሊግ መድመቁን ቀጥሏል

ዛሬ በተከናወነ የ20ኛው ሳምንት የኦማን ጂንዳል ሊግ ጨዋታ አል ሸባብ ተጋጣሚው አል ሳማይልን ሰባት ለባዶ ሲረመርም በድንቅ ወቅታዊ ብቃት የሚገኘው ኢትዮጵያዊው ከነአን ማርክነህም ሀትሪክ ሰርቷል። ከዚህ ቀደምም ቡድኑ አል ካቦራን ሦስት ለባዶ ባሸነፈበት የ15ኛው ጨዋታ ላይ ሦስት ግቦች ማስቆጠር የቻለው ተጫዋቹ በዛሬው ዕለትም ሦስት ግቦችን በማስቆጠር የውድድር ዓመቱ 2ኛ ሀትሪክ ሰርቷል። አርባ አራት ነጥብ በመሰብሰብ 3ኛ ደረጃ ለተቀመጠው አል ሸባብ ወሳኝ ተጫዋች መሆኑን እያስመሰከረ የሚገኘው ከነአን በኦማን ጂንዳል ሊግ ያስቆጠራቸው አስራ ሰባት ግቦች ጨምሮ በውድድሩ ዓመቱ በሁሉም ውድድሮች ሀያ ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

