ሙሉቀን አዲሱ ወደ ሀምራዊ ለባሾቹ አምርቷል

ሙሉቀን አዲሱ ወደ ሀምራዊ ለባሾቹ አምርቷል

ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከወላይታ ድቻ ጋር ጥሩ ቆይታ የነበረው ሙሉቀን አዲሱ የንግድ ባንክ የመጀመርያ ፈራሚ ሆኗል።

በአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ የሚመሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ለከርሞ ውድድር ዓመት ራሳቸውን ለማጠናከር ወደ ዝውውሩ በመግባት ትናንት የአራት ነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል ማራዘማቸው ይታወቃል። ዛሬ ደግሞ የመጀመርያው ቡድኑ የተቀላቀለው ሙሉቀን አዲሱን ለማድረግ መስማማታቸውን አውቀናል።

በነገሌ አርሲ፣ በገላን ከተማ፣ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በአትዮጵያ መድን፣ በሲዳማ ቡና እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት በወላይታ ዲቻ ጥሩ ብቃቱን ያሳየው ሙሉቀን ከዚህ ቀደም በገላን ከተማ አብረውት የሰሩትን አሰልጣኝ በፀሎትን ምርጫው አድርጎ ለንግድ ባንክ ለሁለት ዓመት ለመጫወት ተስማምቷል።