አስራት ቱንጆ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል

አስራት ቱንጆ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል

ያለፉት ሁለት ዓመታት በብርቱካናማዎቹ ቆይታ የነበረው ሁለገብ ተጫዋች ወደ ሌላ የሊጉ ክለብ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

ያለፉትን ሁለት ዓመታት በድሬዳዋ ከተማ ቆይታ የነበረው ሁለገቡ አስራት ቱንጆ ላለፉት ቀናት ካደረጋቸው ድርድሮች በኋላ ወደ ባህር ዳር ከተማ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።  ቀደም ብለው ሽመልስ በቀለ እና ኪቲካ ጅማን ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት የጣና ሞገዶቹ አሁን ደግሞ አስራት ቱንጆን የግላቸው ለማድረግ ከስምምነት ደርሰዋል።  በጅማ አባ ጅፋር ከተጫወተ በኋላ ለስድስት ተከታታይ ዓመታት በኢትዮጵያ ቡና ቆይታ የነበረው አስራት ባለፉት ሁለት ዓመታት በድሬዳዋ ቆይታ ማድረጉ ሲታወስ ከክለብ እግር ኳስ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ማገልገሉ ይታወቃል።