ዐፄዎቹ ወደ ዝውውሩ ገብተዋል

ዐፄዎቹ ወደ ዝውውሩ ገብተዋል

ፋሲል ከነማዎች የዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ ተጫዋች ለማግኘት ከስምምነት ደርሰዋል።

ቀደም ብለው አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስን
ለማስቀጠል የወሰኑት ፋሲል ከነማዎች አሁን ደግሞ ወደ ዝውውሩ በመግባት በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በግሉ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈውን ቁመተ መለሎው ናይጄሪያዊው ጄሮም ኦዴ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

በ2016 የጥር የዝውውር መስኮት ወደ ሀገራችን መጥቶ ለኢትዮጵያ መድን ፣ ባህርዳር ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ መጫወት የቻለው ይህ 1 ሜትር ከ92 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ተጫዋች ከዚህ ቀደም በሱዝ ፣ ስሞሀ ፣ ካናህ እና ኬክሬኔስ የተባሉ የግብፅ ክለቦች መጫወት የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ የፋሲል ከነማ የክረምቱ የመጀመሪያ ፈራሚ ለመሆን ከስምምነት ደርሷል።