ከነገ በስቲያ የሴኔጋል አቻውን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂውን ከፍልሚያው ውጪ አድርጓል።

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አስር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ ሁለተኛ ጨዋታውን የፊታችን ማክሰኞ ከሴኔጋል ጋር የሚያከናውን ሲሆን በዛሬው ዕለትም ባህር ዳር ላይ የመጀመሪያ ልምምዱን አከናውኗል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አሁን ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት ከቡድኑ ተጫዋቾች መካከል አጥቂው መስፍን ታፈሰ ዓርብ በተደረገው የሱዳን ጨዋታ ቢጫ ካርድ ማየቱን ተከትሎ በሁለት ቢጫ ቅጣት ምክንያት ከሴኔጋል ጋር ከሚደረገው ጨዋታ ውጪ ሆኗል።
መስፍን የዛሬው የልምምድ መርሐ ግብር ላይ ሲሳተፍ ብንመለከትም ተጫዋቹ ግን ከወሳኙ የማክሰኞ ጨዋታ ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል።

