የዋልያዎቹ ተጋጣሚ አሰልጣኝ ወደ ሀገራችን ከመምጣታቸው በፊት ኤርፖርት ላይ አስተያየት ሰጥተዋል

የዋልያዎቹ ተጋጣሚ አሰልጣኝ ወደ ሀገራችን ከመምጣታቸው በፊት ኤርፖርት ላይ አስተያየት ሰጥተዋል

የሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቺኪንሆ ኮንዴ ከኢትዮጵያ ጋር ለሚደረገው ወሳኝ ጨዋታ በተስፋ ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ ገለፁ።

​የሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቺኪንሆ ኮንዴ በታንዛኒያ፣ ዩጋንዳ እና ኬንያ በጋራ በሚዘጋጀው የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ለሚያደርጉት የምድብ 10 አራተኛ ጨዋታ በባህር ዳር አወንታዊ ውጤት እንደሚያስመዘግቡ ከፍተኛ ተስፋ እንዳላቸው ተናገሩ።

​አሰልጣኙ ወደ ኢትዮጵያ ከማምራታቸው በፊት በማቫላኔ አውሮፕላን ማረፊያ በሰጡት መግለጫ ባለፈው ዓርብ በሜዳቸው የደረሰባቸው ሽንፈት የትላንት ታሪክ መሆኑን ጠቁመው ተጫዋቾቹ ከአዕምሮ ጫና ወጥተው ለመጪው ጨዋታ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። አሠልጣኙ ​አያይዘውም “እግር ኳስ ስህተትን ለማረም ወይም ለማካካስ ሁልጊዜም ዕድል ከሚሰጡ ጥቂት ሙያዎች አንዱ ነው። በሜዳችን የደረሰብን ሽንፈት ከምንጠብቀው ውጪ ነበር ፤ አሁን ግን አቅማችን በፈቀደው መጠን በኢትዮጵያ ሜዳ አሸንፈን ምላሽ ለመስጠት ጥሩ እድል አለን። ተጫዋቾቹ አርፈዋል ፤ ቤተሰቦቻቸውን ጎብኝተው አዲስ መንፈስ ይዘው ተመልሰዋል” በማለት ተናግረዋል።

​አሰልጣኙ 4-2-3-1 የጨዋታ አሰላለፍ መቀጠሉን ጠቅሰው ከባለፈው አርብ አሰላለፍ የተወሰኑ ለውጦች እንደሚኖሩ አንስተዋል። ከእነዚህም መካከል ከቅጣት መልስ ወደ ቡድኑ የሚቀላቀለው ጊማ ለአማካይ ክፍላቸው ተጨማሪ ጥራት እና መረጋጋት እንደሚሰጥ አመላክተዋል።