ፕሪሚየር ሊግ በ2ኛ ሳምንት ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አዳማ በአሸናፊነታቸው ቀጥለዋል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ ተካሂደው ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አዳማ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ አሸንፈዋል፡፡

አዳማ አበበ ቢቂላ ላይ ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው አዳማ ከተማ 2-0 አሸንፏል፡፡ የመጀመርያው አጋማሽ ያለግብ የተጠናቀቀ ሲሆን አዳማ ከተማዎች የጨዋታው 2/3ኛ ክፍለ ጊዜ ከተገባደደ በኋላ ባስቆጠሯቸው ግቦች አሸንፈው ወጥተዋል፡፡ ባልተለመደ ሁኔታ በአጥቂ ስፍራ የተጫወተው ሙጂብ ቃሲም በ69ኛው ደቂቃ በግራ መስመር ከሱሌይማን የተሻገረውን ቅጣት ምት በግንባሩ በመግጨት ቀዳሚዋን ግብ ሲያስቆጥር በ90ኛው ደቂቃ በተመሳሳይ ከቅጣት ምት ሲሳይ ቶሊ ያሻማውን ኳስ ሚካኤል ጆርጅ በግንባሩ ገጭቶ የአዳማን ሁለተኛ ግብ አስቆጥሯል፡፡

ሁለቱንም የአዳማ ከተማ ግቦች ያስቆጠሩት ሙጂብ ቃሲም እነና ሚካኤል ጆርጅ የቀድሞ የሲዳማ ቡና ተጫዋቾች እንደነበሩ የሚታወስ ነው፡፡

ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2-1 በመርታት የውድድር ዘመኑን የመጀመርያ ድል አሳክቷል፡፡ ኤሌክትሪኮች በፍጹም ገብረማርያም የ4ኛ ደቂቃ ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችሉም ኤርሚያስ በለጠ ከአሳምነው አንጀሎ የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ቡድኖቹ ወደ መልበሻ ክፍል ከማምራታቸው 1 ደቂቃ በፊት ድሬዳዋ ከተማን አቻ አድርጓል፡፡ በ63ኛው ደቂቃ ደግሞ ናሽናል ሴሚንትን ለቆ ዘንድሮ ክለቡን የተቀላቀለው ያሬድ ታደሰ በግሩም የአክሮባቲክ ምት ግብ አሰቆጥሮ ድሬዳዋ ከተማን 3 ነጥብ አስጨብጧል፡፡ በጨዋታው የኤሌክትሪኩ ብሩክ አየለ እና የድሬዳዋው ተስፋዬ ዲባባ በፈጠሩት ፀብ እና የኃይለ ቃል ንግግር በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል፡፡

አርባምንጭ ላይ አርባምንጭ ከ ወልድያ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ አዲስ ከበባ ላይም በተመሳሳይ አዲስ አበባ ከተማ ከ ጅማ አባ ቡና ያለ ግብ በአቻ ውጤት ጨዋታቸውን ፈጽመዋል፡፡ ከከፍተኛ ሊግ ያደጉት አአ ከተማ እና ወልድያ በ2 ጨዋታ 4 ነጥብ በመያዝ መልካም አጀማመር ማድረግ ችለዋል፡፡

img_0171

በአዲሰ አበባ ስታድየም 11:30 ላይ በደደቢት እና ቅዱስ ጊዮርጊስ መካከል የተደረገው የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ በፈረሰኞቹ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለቱም የድል ግቦች በመጀመርያው አጋማሽ የተገኙ ሲሆን ምንተስኖት አዳነ በ24ኛው ፣ አዳነ ግርማ በ45ኛው ደቂቃ የድል ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

ቅዳሜ በተደረገው ብቸኛ ጨዋታ መከላከያ ከ ኢትዮጵያ ቡና 2-2 ሲለያዩ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ሀዋሳ ከተማ እና ፋሲል ከተማ ከ ወላይታ ድቻ በዚህ ሳምንት መካሄድ የነበረባቸውና ወደ ሌላ ጊዜ የተላለፉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡


 የ2ኛ ሳምንት ውጤቶች

[table id=54 /]

የደረጃ ሰንጠረዥ

[league_table 10415]

የ3ኛ ሳምንት ፕሮግራም

[table id=55 /]

ከፍተኛ ግብ አግቢዎች

[player_list 17691]

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *