ሲዳማ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ሲዳማ ቡና 3-1ሐዋሳ ከተማ

9′ በረከት አዲሱ፣ 61′ ፍፁም ተፈሪ፣ 82′ አዲስ ግደይ | 90′ አረፋት ጃኮ


ጨዋታው በሲዳማ ቡና 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል።


91′ የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና

በረከት አዲሱ ወጥቶ አዲስአለም ደበበ ገብቷል።


90′ ጎል!!!!

ደስታ ዩሀንስ ያሻማውን ኳስ በመጠቀም አረፋት ጃኮ ለሐዋሳ ከተማ ግብ አስቆጥሯል።


90′ ተጨማሪ ሰዐት – 3 ደቂቃ


84′ የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና

ሶስተኛውን ግብ ያስቆጠረው አዲስ ግደይ ወጥቶ ኤሪክ ሙራንዳ ገብቷል።


82′ ጎል!!!!

ተቀይሮ የገባው ፀጋዬ ባልቻ በረጅሙ ያሻገረውን አዲስ ግደይ በሚገርም ሁኔታ በሐዋሳ መረብ ላይ በማሳረፍ ልዩነቱን ማስፋት ችሏል።


77′ የተጫዋች ለውጥ – ሲዳማ ቡና

አንበሉ ፍፁም ተፈሪ በጉዳት ሲወጣ ፀጋዬ ባልቻ ተክቶት ገብቷል።


73′ የተጫዋች ለውጥ  – ሐዋሳ ከተማ

አስጨናቂ ሉቃስ ወጥቶ ኤፍሬም ዘካሪያስ ገብቷል።


66′ ሲዳማ ቡና ጫና ፈጥሮ እየተጫወተ ይገኛል።


61′ ጎል!!!!

ትርታዬ ደመቀ ከማዕዘን ምት ያሻገረውን ኳስ ፍፁም ተፈሪ አግኝቶ የሀዋሳን ተከላካዮች ስህተት በመጠቀም የሲዳማ ቡናን ሁለተኛ ግብ አስቆጥሯል።


56′ የተጫዋች ለውጥ – ሐዋሳ ከተማ

ፍርድአወቅ ሲሳይ ወጥቶ አረፋት ጃኮ ገብቷል።


51′ ፍርዳወቅ ሲሳይ መድሀኔ ታደሰ ከመስመር ያሻገረው ኳስ የፈጠረውን ጥሩ የግብ ዕድል አምክኖታል።


47′ የተጫዋች ለውጥ ሐዋሳ ከተማ

መሳይ ፓውሎስ ወጥቶ መድሀኔ ታደሰ ገብቷል።


46′ ሁለተኛው አጋማሽ ክፍለ ጊዜ በሲዳማ ቡና አማካኝነት ተጀመረ።



የመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ  በሲዳማ ቡና 1-0 መሪነት ተጠናቋል።


45′ ተጨማሪ ሰዐት – 1 ደቂቃ


41′ አዲስ ግደይ ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ የግቡን የቀኝ ቋሚ ለትሞ ወጥቷል።


34′ በረከት አዲሱ ኳስ ይዞ በመግባት ወደ ግብ ሞክሮ ወደውጪ ወጥቶበታል።


27′ በስታዲየሙ የሚገኘው ተመልካች ባልተለመደ ሁኔታ ቁጥሩ ከሌላው ጊዜ አንፃር እጅግ ቀንሷል።


23′ አዲስ ግደይ በአንድ ሁለት ቅብብል ከትርታዬ ደመቀ ጋር ተጫውቶ በማለፍ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ሶሆሆ ሜንሳ አውጥቶታል።


20′ እሰራኤል እሸቱ የግሉን ጥረት ተጠቅም ያቀበለውን ኳስ ፍሬው ሰለሞን ከግብ ጠባቂው ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ መጠቀም አልቻለም።


17′ በረከት ከመሰመር በቀጥታ ወደግብ የመታው ኳስ ወደ ውጭ ወጥቷል። ሲዳማ ቡናዎች ተጨማሪ ግብ ለማግኘት ጫና ፈጥረው እየተጫወቱ ይገኛሉ።


9′ ጎል!!!!

በረከት አዲሱ አዲስ ግደይ በግሩም ሁኔታ ከመስመር ያሻገረለትን ኳስ ወደግብ በመቀየር ሲዳማን መሪ አድርጓል።


1′ ጨዋታው በሀዋሳ ከተማ  አማካኝነት ተጀመረ።


የሲዳማ ቡና አሰላለፍ

1. ፍቅሩ ወዴሳ

15. ሳውሬል ኦልርሽ– 4. አንተነህ ተስፋዬ – 21. አበበ ጥላሁን — 32. ሳንደይ ሙቱኩ

2 ወሰኑ ማአዜ – 20. ሙሉአለም መስፍን — 8. ትርታዬ ደመቀ — 5. ፍፁም ተፈሪ

14. አዲስ ግደይ — 9 በረከት አዲሱ


ተጠባባቂዎች

30 መሳይ አያና

 12ግሩም አሰፋ

 23 ሙጃይድ መሀመድ

 19 አዲስ አለም ደበበ

 11 ፀጋዬ ባልቻ

 27 ላኪ ሳኒ

13 ኤሪክ ሙራንዳ



የሀዋሳ ከተማ አሰላለፍ 

 1.ሶሆሆ ሜንሳ

12.ደስታ ዮሀንስ –  22.መላኩ ወልዴ 26.ወንድማገኝ ማህረግ – 4. አስጨናቂ ሉቃስ

24.ሀይማኖት ወርቁ – 5.ታፈሰ ሰለሞን – 27. ፍርዳወቅ ሲሳይ– 10.ፍሬው ሰለሞን  

9. እስራኤል እሽቱ


ተጠባባቂዎች

30 አላዛር መርኔ

15 አረፋት ጃኮ

14 ወንድሜነህ አይናለም

3 ኤፍሬም ዘካሪያስ

17 መድሀኔ ታደሰ

29 ለይኩን መርደኪዮስ

30 ነጋሽ ታደሰ‎

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *