ኢትዮ ኤሌክትሪክ 2-1 ወላይታ ድቻ | የአሰልጣኞች አስተያየት 

ብርሃኑ ባዩ – ኢትዮ ኤሌክትሪክ

ስለ ጨዋታው

” በመጀመሪያው አጋማሽ እኛ የተሻልን ነበርን፡፡ በዚህም እኛ ብዙ ወደ ጎል የቀረቡ እድሎችን አምክነናል ፤ እነዛን እድሎች አስቆጥረን ቢሆን ኖሮ ወደ መጨረሻ ላይ እንደታየው ጫና ውስጥ ላንገባ እንችል ነበር፡፡”

ስለ በሀይሉ ተሻገር ሚና

” ጥሩ ነው በሃይሉ በዛሬው ጨዋታ በዳዊት አለመኖር ምክንያት ተጠቅመዋል ፤ ጥሩ መንቀሳቀስም ችሏል፡፡”

አሸናፊነትን ስለማስቀጠል

“በሜዳችንም ሆነ ከሜዳችን ውጪ በምናደርጋቸው ጨዋታዎች ተበልጠን ተሸንፈን አናውቅም ፤  በተመሳሳይ አቻ በወጣንባቸው 7 ጨዋታዎች በልጠን በርካታ የግብ እድሎችን ፈጥረን ኳስና መረብን የማገናኘት ችግር ካልሆነ በስተቀር ኤሌክትሪክ በዘንድሮ የውድድር አመት ተበልጦ የተሸነፈበት ጨዋታ የለም፡፡ ኳስና መረብን የማገናኘት እና በቀላሉ ግብ የማስተናገድ ችግር  ካስተካከልን ቡድኑን ምንም የሚያሰጋው ነገር የለም፡፡”

መሣይ ተፈሪ – ወላይታ ድቻ

ስለ ጨዋታው

” በመጀመሪያው አጋማሽ እንደፈለግነው መጫወት አልቻልንም ፤ በሁለተኛውም አጋማሽ ተጋጣሚያችን በተከታታይ ነጥብ በመጣላቸው የተነሳ አለመረጋጋቶች ነበሩ ፤ ፈጣሪ ይመስገን አልተሳካም፡፡”

በሁለተኛው አጋማሽ መጨረሻ ደቂቃዎች ላይ ጫና ስለመፍጠራቸው

“ብዙ ጊዜ የሚመራ ቡድን ባህሪ ይህ ነው ፤ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም እንደሚባለው ያለህን ሰጥተህ ትጫወታለህ፡፡ ነገርግን ቢሆን የሚመረጠው ከመጀመሪያው ጀምሮ አጥቅተህ መጫወት ነው፤ እንደሚታወቀው በእግርኳስ ያገባ ቡድን ውጤት ለማስጠበቅ የማፈግፈግ እንዲሁም የተመራው ለማግባት ደግም ተጭኖ ለመጫወት የሚያደርጉት ጥረት በስፋት ይታይበታል፡፡”

ከሜዳ ውጪ ነጥብ ስለመጣል

“የሜዳችንን አድቫንቴጅ በሚገባ እየተጠቀምን እንገኛለን ፤ ነገር ከሜዳ ውጪ ውጤታችን ጥሩ አይደለም ይህንንም ለመቅረፍ ጥረት እናደርጋለን፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *