ወልቂጤ ከተማ የሁለት ተጫዋቾችን ውል አራዝሟል

በዝውውር መስኮቱ የዘገዩ ቢመስሉም የጌታነህ ከበደን ጨምሮ በርከት ያሉ ወሳኝ ዝውውሮችን የፈፀሙት ወልቂጤ ከተማ የሁለት ተከላካዮችን ውል ለአንድ ተጨማሪ ዓመት አራዝሟል፡፡

የቀድሞው የባህርዳር ከተማ፣ ደቡብ ፖሊስ፣ አዳማ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጫዋች የሆነው ዮናስ በርታ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አጋማሽ ኤሌክትሪክን በመልቀቅ ወደ ወልቂጤ ማምራቱ ይታወሳል፡፡ ከተከላካይ አማካይነት ወደ ተከላካይ ስፍራ ከመጣ በኋላ ጥሩ ጊዜን ያሳለፈው ተጫዋቹ ተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለመቆየት ውሉ ታድሶለታል፡፡

የመስመር ተከላካዩ ዮናታን ፍሰሐ በወልቂጤ ውሉን ያደሰ ሌላኛው ተጫዋች ሆኗል፡፡ ከአዳማ ከተማ የተገኘው እና በሲዳማ ቡና ተጫውቶ ያሳለፈው ይህ ወጣት ተከላካይ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አጋማሽ ላይ ወደ ወልቂጤ ማምራቱ የሚታወስ ሲሆን ለተጨማሪ ዓመት ውሉን አድሷል፡፡