ሮበርት ኦዶንግካራ መንገሱን ቀጥሏል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ትላንት ፍጻሜውን ሲያገኝ እንዳለፉት አመታት ሁሉ የኮከብ ግብ ጠባቂነት ክብሩ ወዴት እንደሚሄድ ሁሉም እርግጠኛ ሆኗል፡፡ ዩጋንዳዊው ግብ ጠባቂ ለአራተኛ ተከታታይ አመታት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ምርጡ ግብ ጠባቂ ተብሎ ተሸልሟል፡፡ የዋንጫ እና 15 ሺህ ብር ሽልማቱንም ትላንት ተረክቧል፡፡

ሮበርት ኦዶንግካራ በኢትዮጵያ በተጫወተባቸው 4 ሙሉ የውድድር ዘመናት ኮከብነትን ሲያገኝ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ከፈረመበት የ2003 የውድድር ዘመን አጋማሽ ጀምሮ የ2003 2ኛ ግማሽ የውድድር ዘመን ምንም ግብ ሳያስተናግድ ሪኮርዱንም ጨብጧል፡፡

በ2003 የተጀመረው የኮከብ ግብ ጠባቂዎች ምርጫ ይህንን ይመስላል

2003 – ሲሳይ ባንጫ – ሲዳማ ቡና

2004 – ሮበርት ኦዶንግካራ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

2005 – ሮበርት ኦዶንግካራ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

2006 – ሮበርት ኦዶንግካራ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

2007 – ሮበርት ኦዶንግካራ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *