የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ትላንት ሲጠናቀቅ በብዙዎች ግምት ተሰጥቶት የነበረው በኃይሉ አሰፋ የ2007 የውድድር ዘመን ኮከብ ተጫዋችነት ክብርን አግኝቷል፡፡
ዘንድሮ የቅዱስ ጊዮርጊስ አቋም በሚዋዥቅበት ወቅት እንኳን ድንቅ ብቃቱን ሲያሳይ የነበረው ቱሳ የልፋቱን ዋጋ በአመቱ መጨረሻ አሳክቷል፡፡ ፈጣኑ የመስመር አማካይ አመዛኙ የቅዱስ ጊዮርጊስ ግቦች መነሻ የነበረ ሲሆን አብዛኛዎቹ ተሸጋሪ ኳሶቹ ልኬታቸውን የጠበቁ ነበሩ፡፡
ከ3 የተለያዩ ክለቦች ጋር የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ በማንሳት ባለታሪክ የሆነው ‹‹ቱሳ›› ትላንት ምሽት የኮከብነት ሽልማቱን ሲቀበል የደስታ እንባ አንብቷል፡፡
በኃይሉ አሰፋ ሊጉ እንደ አዲስ ከተጀመረበት 1990 በኋላ የኮከብነት ሽልማት የወሰደ 13ኛው ተጫዋች መሆን ሲችል 6ኛው የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች መሆንም ችሏል፡፡
ከ1990 ወደህ የሊጉ ኮከብነትን የወሰዱ ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1990.አንዋር ያሲን(መብራት ኃይል)
1991.አህመድ ጁንዲ(ምድር ባቡር)
1992.አንዋር ሲራጅ(መብራት ኃይል)
1993.አሸናፊ ግርማ(ኢትዮጵያ ቡና)
1994.ሙሉአለም ረጋሳ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
1995.አሸናፊ ግርማ(ኢትዮጵያ ቡና)
1996.ሙሉጌታ ምህረት(ሀዋሳ ከነማ)
1997.ደጉ ደበበ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
1998.ቢንያም አሰፋ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2000. ታፈሳ ተስፋዬ(ኢትዮጵያ ቡና)
2001.ጌታነህ ከበደ(ደቡብ ፖሊስ)
2002. ጀማል ጣሰው(ደደቢት)
2003. አዳነ ግርማ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2004. ደጉ ደበበ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2005. ጌታነህ ከበደ (ደደቢት)
2006 – ኡመድ ኡኩሪ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2007. በኃይሉ አሰፋ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)