ባለታሪኩ ሳሙኤል ሳኑሚ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንደአዲስ ከተጀመረበት 1990 ወዲህም ሆነ ባለፉት 71 አመታት የሊጉ ታሪክ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ተጫዋች ኮከብ ግብ አግቢ ሆኖ አያውቅም፡፡ ናይጄርያዊው የመስመር አጥቂ ሳሙኤል ሳኑሚ ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን ይህንን ታሪክ ለውጧል፡፡

በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ደደቢት የተዛወረው ሳሙኤል በፈረሰኞቹ እና ከዛም ቀደም በኤሌክትሪክ አገልግሎቱ በመስመር አማካይነት ሲገደብ ቆይቶ በሰማያዊዎቹ ቤት ሁነኛ ግብ አግቢ ሆኗል፡፡ በውድድር ዘመኑ 2 ሐት-ትሪኮችን በመስራት የግብ መጠኑን 22 አድርሶ በ2005 ጌታነህ ከበደ በደደቢት ማልያ ካስቆጠራቸው 22 የሊግ ግቦች ጋር መስተካከል ችሏል፡፡

ሳኑሚ ትላንት ምሽት ከዋንጫ እና 25ሺህ ብር ሽልማቱ በኋላ በሰጠው አስተያየት ጠንካራ ስራ ለስኬት እናዳበቃው ተናግሯል፡፡

‹‹ ቀላል ነገር አይደለም፡፡ ፈጣሪዬን ለዚህ ክብር ስላበቃኝ አመሰግነዋለሁ፡፡ በጉዳት የተወሰኑ ጨዋታዎች ቢያምለጡኝም ተስፋ ሳልቆርጥ ጠንክሬ ሰርቻለሁ፡፡ ለስራህ መስዋእት የምትከፍል ከሆነ የምትፈልገውን ታገኛለህ፡፡ ዘንድሮ ያገኘሁት ክብር በኢትዮጵያ የመጀመርያዬ ነው፡፡ ይህንን ስላገኘሁ አልተኛም፡፡ በቀጣይ አመት ከዚህ የተሻለ ክብር ማሳካት እፈልጋለሁ፡፡ ›› ብሏል፡፡

ሳኑሚ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ20 ግቦች በላይ ከመረብ ያሳረፈ —ኛው ተጫዋች መሆን ችሏል፡፡ ከሱ በላይ በአንድ የውድድር ዘመን ከፍተኛ ግብ ማስቆጠር የቻሉትም ዮርዳኖስ አባይ(24) ፣ ታፈሰ ተስፋዬ እና አዳነ ግርማ (23) ብቻ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በ1990 ሊጉ በአዲስ መልክ ከተጀመረ ወዲህ ኮከብ ግብ አግቢዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

1990 – ሀሰን በሽር(መድን)-8

1991 – በረከት ሀጎስ(ሀዋሳ ከነማ)-8

1992 – ስንታየሁ ጌታቸው(ቅዱስ ጊዮርጊስ)-8

1993 – ዮርዳኖስ አባይ(መብራት ኃይል)-24

1994 – ዮርዳኖስ አባይ(መብራት ኃይል)-20

1995 – ዮርዳኖስ አባይ(መብራት ኃይል/ኢትዮጵያ ቡና)-14

አህመድ ጁንዲ(ምድር ባቡር)-14

1996 – መሳይ ተፈሪ (አርባምንጭ ጨጨ)-13

1997 – መዳህኔ ታደሰ(ትራንስ ኢ.)-18

1998 – ታፈሰ ተስፋዬ(ኢትዮጵያ ቡና)-21

1999 – ታፈሰ ተስፋዬ (ኢትዮጵ ቡና) 11 (10 ክለቦች አቋርጠው እስኪወጡ ድረስ)

2000 – ሳላዲን ሰኢድ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)-21

2001 – ታፈሰ ተስፋዬ(ኢትዮጵያ ቡና)-23

2002 – ታፈሰ ተስፋዬ(ኢትዮጵያ ቡና)21

2003 – አዳነ ግርማ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)-20

ጌታነህ ከበደ(ደደቢት)-20

2004 – አዳነ ግርማ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)-23

2005 – ጌታነህ ከበደ (ደደቢት) – 22

2006 – ኡመድ ኡኩሪ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) – 16

2007 – ሳሙኤል ሳኑሚ (ደደቢት) – 22

(C) Soccerethiopia.net

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *