አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ትላንት ፍፃሜውን ባገኘው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ዋንጫውን ሲያነሱ ነግላቸውም የሊጉ ኮከብ አሰልጣን ክብርን አግኝነተዋል፡፡ በፌዴሬሽኑ ደንብ መሰረት የቻምፒዮኑ ቡድን አሰልጣኝ በመሆናቸው ይህንን ክብር ያገኙት አሰልጣኝ ፋሲል ከትላንቱ ጨዋታ ፍፃሜ በኋላ በሰጡት አስተያየት አሁን ደስታቸውን የሚያጣጥሙበት ሰአት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
‹‹ በቀጣይ አመት በሚካፈልባቸው ውድድሮች ውጤት ለማምጣት ክለቡ የቤት ስራውን ከአሁን ጀምሮ ይሰራል፡፡ ዛሬ ግን ደስታውን ነው ማጣጣም የምፈልገው፡፡ ድል የልፋት ውጤት ስለሆነ ሁሌም ያስተስተኛል፡፡ ›› ብለዋል፡፡
የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ምድን እና መከላከያ የመስመር ተከላካይ በ1991 እና 1992 ክለቡ የሊጉን ዋንጫ ሲያነሳ የክለቡ አምበል የነበሩ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ በዋና አሰልጣንነት ይህንን ክብር በማግኘት ፕሪሚየር ሊጉ በ1990 እንደአዲስ ከተጀመረ ወዲህ የሊጉን ዋንጫ በተጫዋችነት እና አሰልጣኝነት ያሳኩ የመጀመርያው አሰልጣኝ ለመሆን በቅተዋል፡፡
ከአሰልጣን ፋሲል በፊት የነበሩት ባለድል አሰልጣኞች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1990 – ሀጎስ ደስታ(መብራት ኃይል)
1991 – አስራት ኃይሌ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
1992 – አስራት ኃይሌ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
1993 – ጉልላት ፍርዴ(መብራት ኃይል)
1994 – ስዩም ከበደ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
1995 – ስዩም ከበደ(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
1996 – ከማል አህመድ(ሀዋሳ ከነማ)
1997 – ስሬድዮቪች ሚሉቲን ‹ሚቾ›(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
1998 – ስሬድዮቪች ሚሉቲን ‹ሚቾ›(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
1999 – ከማል አህመድ(ሀዋሳ ከነማ
2000 – ስሬድዮቪች ሚሉቲን ‹ሚቾ›(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2001 – ስሬድዮቪች ሚሉቲን ‹ሚቾ›(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2002 – ስሬድዮቪች ሚሉቲን ‹ሚቾ›(ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2003 – ውበቱ አባተ(ኢትዮጵያ ቡና)
2004 – ዳንኤሎ ፒየርሉዊጂ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2005 – ንጉሴ ደስታ (ደደቢት)
2006 – ሬኔ ፌለር (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2007 – ፋሲል ተካልኝ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
(C) Soccerethiopia.net