​መከላከያ 2 ተጫዋቾች ሲያስፈርም የአዲሱ ተስፋዬን ውል አድሷል

በዝውውር መስኮቱ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው መከላከያ አማኑኤል ተሾመ እና አቅሌሲያስ ግርማን አስፈርሟል፡፡

በ2007 ክረምት አዲስ አበባ ከተማን ለቆ ወደ ወላይታ ድቻ በማምራት ሁለት የውድድር ዘመናት በሶዶው ክለብ ያሳለፈው አማኑኤል ወደ ጦሩ በሁለት አመት ኮንትራት ያደረገው ዝውውር በየጨዋታው ተመሳሳይ የአማካይ ክፍል ጥምረት ለሚጠቀመው መከላከያ አማራጭ የሚፈጥርለት ይሆናል፡፡

አመቱን በጅማ ያሳለፈውና ክለቡ ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲሸጋገር ቁልፍ ሚና የተጫወተው አቅሌሲያስ ግርማ ሌላው ክለቡን የተቀላቀለ ተጫዋች ነው፡፡ የቀድሞው የድሬዳዋ ከተማ እነና ወሎ ኮምቦልቻ አጥቂ ከመከላከያ የለቀቀው የባዬ ገዛኸኝን ክፍተት ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በክረምቱ ዝውውር መስኮት ለተለያዩ ክለቦች ለመፈረም ተቃርቦ የነበረው አዲሱ ተስፋዬ በመጨረሻም ከመከላከያ ጋር ያለውን ውል ለተጨማሪ ሁለት አመታት አድሷል፡፡ ወላይታ ድቻን ለቆ ወደ መከላከያ በማምራት ለሁለት አመታት ክለቡን ያገለገለው አዲሱ ከፍተኛ መሻሻል እያሳዩ ከሚገኙ የሊጉ ተከላካዮች አንዱ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *