​ፋሲል ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን አስፈረመ

ፋሲል ከተማ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ማስፈረሙን በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አስታውቋል፡፡ ዳዊት እስጢፋኖስ እና ብሩክ ግርማ ክለቡን የተቀላቀሉ ተጨዋቾች ናቸው፡፡

ዳዊት እስጢፋኖስ የአንድ አመት የኤሌክትሪክ ውሉን አጠናቆ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ለማምራት ከስምምነት ላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም በግል ጉዳይ ምክንያት ክለቡን ሳይቀላቀል ቀርቶ ወደ ፋሲል ከተማ አምርቷል፡፡ የሰለሞን ገብረመድህን መልቀቅን ተከትሎ የማጥቃት እንቅስቃሴን የሚመራ ተጫዋች እጥረት የነበረበት የአጼዎቹ የአማካይ ክፍል በዳዊት መምጣት ይጠናከራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ብሩክ ግርማ ሌላው የክለቡ ፈራሚ ነው፡፡ በከፍተኛ ሊጉ ለኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ሲጫወት የነበረው ብሩክ በቀኝ መስመር ተከላካይ ስፍራ ላይ ሰኢድ ሁሴን በማይኖርባቸው ጨዋታዎች ላይ አማራጭ ይፈጥራል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *