ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድኑ ከነገው ጨዋታ በፊት የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ ሰርቷል

በ2018 ፈረንሳይ ለምታስተናግደው ከ20 አመት በታች የአለም ዋንጫ የመጀመርያ የደርሶ መልስ ማጣሪያ ጨዋታውን ከኬንያ ጋር የሚያደርገው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከነገው ጨዋታ በፊት የመጨረሻ የሆነውን ልምምድ ዛሬ ጨዋታው በሚከናወነበት ሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታድየም አከናውኗል፡፡

አሰልጣኝ ቴዎድሮስ ደስታ ከነሀሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ ቡድኑን ሲያዘጋጁ የቆዩ ሲሆን ከአጥቂዋ ትደግ ፍስሀ በቀር ሁሉም በሙሉ ጤንነት ለጨዋታው ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የቡድኑ አሰልጣኝ ቴዎድሮስ ደስታ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት ጨዋታውን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡ ” ጨዋታውን በሜዳችን እንደማድረጋችን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንገባለን፡፡ የዝግጅት ቀን ማነስ ተፅዕኖ ሊያደርግብን ቢችልም በሳቢ ጨዋታም እንኳ ባይሆን የማሸነፍ ስሜትን ሰንቀን እንገባለን፡፡ ” ብለዋል፡፡

ጨዋታው ነገ (እሁድ) 10:00 ሰአት ላይ በሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም ሲደረግ ዩጋንዳዊያን ዳኞች ጨዋታውን እንደሚመሩት ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *