​አዳማ ከተማ ደቡብ ሱዳናዊ አጥቂ አስፈረመ

በአዳማ ከተማ ያለፉትን ሳምንታት የሙከራ ጊዜ ሲያሳልፍ የነበረው ደቡብ ሱዳናዊው የመስመር አጥቂ ፒተር ዱስማን በቆይታው ክለቡን ማሳመን በመቻሉ በቋሚነት ፊርማውን አኑሯል፡፡

ዱስማን በዬኢ ሴንትራል በ32 ጨዋታዎች 28 ጎሎችን ማስቆጠሩን ተከትሎ ወደ ሀገሪቱ ትልቅ ክለብ አትላባራ ካመራ በኋላ ባለፉት ሶስት የውድድር ዘመናት የቡድኑ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ መሆን ችሏል፡፡ ለደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ቡድንም በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያዎች ላይ ተጫውቷል፡፡

ዱስማን ለአዳማ መፈረሙን ተከትሎ በክረምቱ ውሉን ካራዘመው ኮንጓዊው ጃኮ ፔንዜ በመቀጠል በቡድኑ ውስጥ ሁለተኛው የክለቡ የውጪ ዜጋ ሆኗል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *