ዮሀንስ ሳህሌ ወደ መቐለ ከተማ?

በሳምንቱ መጀመርያ አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትን ከኃላፊነታቸው ያሰናበተው መቐለ ከተማ ዮሀንስ ሳህሌን ቀጣዩ የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ተነግሯል፡፡ በዛሬው እለትም ቡድኑን ልምምድ ሲያሰሩ ታይተዋል፡፡

ከረጅም ጊዜያት የዩናይትድ ስቴትስ ቆይታ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ከ2006 ጀምሮ የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን፣ ደደቢት እና ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ያሰለጠኑት አሰልጣኝ ዮሀንስ በ2009 መጀመርያ ለ2ኛ ጊዜ ለማሰልጠን ወደ ደደቢት ቢመለሱም ከሁለት የሊግ ጨዋታዎች በኋላ ተሰናብተው ለረጅም ወራት ከአሰልጣኝነት ስራ ተገልለው ቆይተዋል፡፡

የአሰልጣኝ ዮሀንስን መሾም መቐለ ከተማ በይፋ ማረጋገጫ ያልሰጠ ሲሆን ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ አካባቢ የተለያዩ መረጃዎችን አግኝታለች፡፡ አንደኛው አሰልጣኙ ቡድኑን ለማሰልጠን መስማማታቸውን ሲገልፅ ሌላኛው መረጃ ደግሞ አሰልጣኙ ቡድኑን በመጀመርያ ተመልክተው ከውሳኔ ላይ ለመድረስ ተስማምተው በሙከራ ደረጃ ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል፡፡

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *