​የኦሮሚያ ዋንጫ የሰበታ ምድብ ዛሬ ተጀመረ

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ሊግ እና አንደኛ ሊግ ክለቦችን የሚያሳትፈውና በ4 ከተሞች ተከፍሎ የሚደረገው የኦሮሚያ ዋንጫ የሰበታ ምድብ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

08፡00 ላይ ለገጣፎ ለገዳዲን ከኢትዮጵያ መድን ያገናኘው ጨዋታ በለገጣፎ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ በርከት ያለ የሰበታ ከተማ ስፖርት አፍቃሪ በታደመበት ጨዋታ የአሰልጣኝ ደረጄ በላይ ኢትዮጵያ መድን በአዲስ ስብስብ ብቅ ሲልየያሬድ ቶሌራው ለገጣፎ በከፊል አዲስ ቡድን ይዞ ቀርቧል፡፡

ጥቂት የጎል ሙከራዎች በታዩበት በዚህ ጨዋታ በ72 ኛው ደቂቃ ሐብታሙ ፍቃደ በግራ መስመር ያሻገረው ኳስ ኄኖክ ታደሰ ወደግብነት ለውጦ ለገጣፎን ባለ ድል አድርጓል፡፡


በቀጣይ የተደረገው የሰበታ ከተማ እና የጅማ አባቡና ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ከመጀመሪያው አንስተው ተጭነው የተጫወቱት ባለሜዳዎቹ ሰበታ ከተማዋች ከርቀት በሚመቱ ኳሶች የአባ ቡና ግብ ቢፈትሹም ግብ ሳይቆጠር የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡
ከዕረፍት መልስ በ46ኛው ደቂቃ ሰበታ ከተማ ዜናው ፈቀደ ባስቆጠረው ግብ መሪ መሆን ቢችልም በ58ኛው ደቂቃ ላይ ጅማ አባቡና በሱራፌል አወል ግብ አማካይነት አቻ መሆን ችሏል፡፡

የኦሮሚያ ዋንጫ ማክሰኞ ቀጥሎ በ 8፡00 ሰበታ ከተማ ከ ለገጣፎ ለገዳዲ  ፤ በ 10፡00 ጅማ አባቡና ከ ኢትዮጵያ መድን ይገናኛሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *