​የእለቱ ዜናዎች | ሀሙስ ጥቅምት 23 ቀን 2010

የሲዳማ ቡና ቅሬታ

“የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሪምየር ሊጉ በተያዘለት ጊዜ ይጀመራል በማለቱ ወደ አዲስ አበባ ከመጣን በኋላ ጨዋታው ወደ ሌላ ጊዜ ተላልፏል መባሉ አላስፈላጊ ወጪ እንድናወጣ አድርጎናል ፣ በቡድኑ ላይም ከፍተኛ የሆነ ድካም ፈጥሯል” ሲል ክለቡ ለሶከር ኢትዮዽያ ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ ላልታወቀ ጊዜ መሸጋገሩ ይታወሳል፡፡

ስፖርታዊ ጨዋነት

የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን የደጋፊዎች ማህበር በስፖርታዊ ጨዋነት እና በስታድየሞች ሰላምን ለማስፈን ከሚመለከታቸው አካላት እና ከደጋፊዎች ጋር የውይይት መድረክ ዛሬ በኢትዮዽያ ሆቴል የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት አቶ ጁነይዲ፣ የፌዴሬሽኑ የሊግ ኮሚቴ ኃላፊዎች፣ አአ የሚገኙ የክለብ ደጋፊዎች፣ የፀጥታ አካላት አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ለስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል  መንስኤው ምድነው?  መፍቴውስ? በሚል ከተሳታፊዎች ጠቃሚ ሀሳቦች በስፋት በማንሳት ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን እንደዚህ ያሉ መድረኮች ወደፊትም በተደጋጋሚ ይዘጋጃሉ ተብሏል፡፡

ከተነሱ የመፍትሄ ሀሳቦች መካከል ቅዱስ ጊዮርጊስን መጥላት ኢትዮዽያ ቡናን መውደድ አይደለም ፣ ኢትዮዽያ ቡናን መጥላት ቅዱስ ጊዮርጊስን መውድደ አይደለም። ፤ ክለቡን በበላይነት የሚመሩት የሁለቱ ክለቦች ( የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮዽያ ቡና)  አመራሮች በመቀራረብ ይወያዩ ፤ ወደ ሜዳ ስንመጣ የለበስነውን ማልያ ልናከብር ይገባል፡፡ ስድብን ከሜዳ ለማራቅ እየለፉ ላሉት አስጨፋሪ ደጋፊዎች እንታዘዝ የሚሉ ይገኙበታል፡፡

ቻን 2018

በቻን ውድድር ማጣርያ ከኢትዮዽያ ጋር የመጀመርያ ጨዋታዋን አአ ላይ የምታደርገው ሩዋንዳ የልዑካን ቡድኗ ዛሬ አአ ይገባል ተብሎ ቢጠበቅም የቪዛ ጉዳይ በተሟላ ሁኔታ ባለመጠናቀቀቁ ምክንያት ነገ ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ተገደዋል፡፡ በርከት ያለ የልዑካን ቡድን በመያዝ እንደሚመጡም ሰምተናል፡፡

በተያያዘ ዜና የእሁዱን ጨዋታ የሚመሩት አራቱም ዳኞች ከጅቡቲ እንደሆነ ሲታወቅ የጨዋታው ኮሚሽነር ከኡጋንዳ እንደሆነ ታውቋል ።

ሲዳማ ቡና ሴቶች

የሲዳማ ቡና የሴቶች ቡድን ዝግጅቱን እስካሁን እንዳልጀመረ ከዚህ ቀደም መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ አሁን ከይርጋለም እንደሚሰማው ከሆነ የሲዳማ የሴቶች ቡድኑ በአሰልጣኝ ፍሬው ወ/ገብርኤል እየተመሩ ዝግጅታቸውን እንደጀመሩ ሰምተናል።

ነቀምት ከተማ

በ2009 የውድድር አመት በከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊ የነበረው ነቀምት ከተማ በውድድር አመቱ ባስመዘገበው ዝቅተኛ ውጤት መሰረት ወደ 1ኛ ሊጉ መውረዱ ይታወቃል። ሆኖም ኢትዮዽያ ንግድ ባንክ በመፍረሱ ምክንያት በከፍተኛ ሊጉ ንግድ ባንክን ተክቶ ምድብ ሀ ላይ እንዲጫወት ፌዴሬሽኑ ወስኗል። በዚህም መሰረት ህዳር 9 በሚጀምረው የከፍተኛ ሊግ ውድድር ነቀምት ከተማ የመጀመርያውን ጨዋታ በሜዳው ወሎ ኮምቦልቻን የሚያስተናግድ ይሆናል።

የስታድየም መግቢያ ትኬት

የኢትዮዽያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ‘ክፍያ ፋይናሻል ቴክሎኖጂ’ ከተሰኘ ተቋም ጋር በመተባበር የትኬት አቆራረጥ አሰራሩን ለመለወጥ ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቆ በሙከራ ላይ እንደሚገኝ የፌዴሬሽኑ የማርኬቲንግ ዳሬክተር አቶ ኢሳይያስ ታፈሰ ለሶከር ኢትዮዽያ ተናግረዋል። የአሰራር ለውጡ የትኬት አጠቃቀሙን ከማኑዋል ወደ ኤሌክትሮኒስ የሚቀይር ሲሆን በዚህም ምክንያት ብዙ ለውጦች ይኖራሉ፡፡ በዚህ ለውጥ ውስጥ  በትልቅ ጨዋታዎች በሚኖሩ ጊዜ የሚፈጠሩ ረጃጅም ሰልፎች እና የሚጭበረበሩ ትኬቶችን ያስቀራል ፣ በረጅም ሰልፍ ምክንያት የሚገላቱ የሚጨናነቁ የህፃናት ፣ የሴቶች ፣ በዕድሜ የገፉ ሰዎችን  ድካምንም ይቀንሳል ተብሏል።

“ትኬቱ ላይ የዕለቱ ጨዋታ ማን ከማን እንደሆነ ፣ ቀኑን እና የሚገቡበት በር ስም ይኖረዋል፡፡ ይህ የትኬት ማጭበርበርን ይቀንሳል፡፡ ከቆረጠበት በር ውጭ በሌላ ቦታ አይገባም ማለት ነው። ትኬቱ የሚሸጥበት መንገድ በሞባይል፣ በኢንተርኔት፣ በተዘጋጁ የትኬት መሸጫ ቦታ በኤጀንቶች አማካኝነት ካሉበት ቦታ ሆነው መግዛት የሚቻልበት አማራጭም ይኖረዋል። ሲስተሙ አሁን ሙሉ ለሙሉ ስራውን ያልጀመረ ሲሆን በጊዜዊነት የተመልካቹን ፍላጎት ለማወቅ በማንዋሉ ላይ የተለያዩ ለውጦች በማድረግ እየሰራ እንደሆነ ገልፀውልናል።

እድሉ ደረጄ

አሰልጣኝ እድሉ ደረጄ በ1ኛ ሊግ የሚሳተፈው የሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ። ኢትዮዽያ ቡና ከ13 አመታት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የሊግ ዋንጫ ሲያነሳ የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች እና አምበል የነበረው እድሉ እግርኳስ ካቆመ በኋላ በኢትዮዽያ ቡና ተስፋ ቡድን አሰልጣኝነት፣ በዋናው ቡድን ረዳት እና ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት እንዲሁም በቡድን መሪነት ማገልገሉ ይታወሳል፡፡

ደቡብ ካስቴል ዋንጫ

በሆሳዕና ከተማ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘውና የደቡብ የከፍተኛ ሊግ ክለቦችን ያሳተፈው የደቡብ ካስቴል ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ነገ ሐርብ በአቢዮ ኤርሳሞ ስታድየም ይደረጋሉ፡፡

07:00 ሀላባ ከተማ ከ ደቡብ ፖሊስ

09:00 ሀዲያ ሆሳዕና ከ ቤንች ማጂ ቡና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *