​በሴቶች ፕሪምየር ሊግ 1ኛ ዲቪዚዮን ተስተካካይ ጨዋታ ኤሌክትሪክ አሸንፏል 

በኢትዮዽያ ከ17 አመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ምክንያት በሁለተኛ ሳምንት መካሄድ የነበረበት የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ተሸጋግሮ ዛሬ የተደረገ ሲሆን ዛሬ በአአ ስታድየም ተካሂዶ ኢትዮ ኤሌክትሪክ 2-1 አሸንፏል።
ብዙም ጠንካራ ፉክክር ባልታየበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከእረፍት በፊት ጤናዬ ወመሴ  እና  አለምነሽ ገረመው በግሩም የቅጣት ምት ባስቆጠሩት ጎል በመምራት ወደ መልበሻ ክፍል ሲያመሩ በሁለተኛው አጋማሽ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት ፈረሰኞቹ ከመሸነፍ ያልዳኑበትን ጎል በተጨማሪ ደቂቃ ላይ መሰሉ አበራ አማካኝነት አስቆጥረው ጨዋታው በኤሌክትሪክ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

የደረጃ ሰንጠረዥ

ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች

የ3ኛ ሳምንት መርሀ ግብር

ቅዳሜ ታህሳስ 14 ቀን 2010

10:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ መከላከያ (ድሬዳዋ)

እሁድ ታህሳስ 15 ቀን 2010

09:00 ደደቢት ከ ሲዳማ ቡና (አአ)

09:00 አዳማ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ (አዳማ)

ሰኞ ታህሳስ 16 ቀን 2010

09:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀዋሳ ከተማ (አአ)

11:00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ጌዲኦ ዲላ (አአ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *