የሐምሌ 22 አጫጭር ዜናዎች

 

በድሬዳዋ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የብሄራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ሁሉም ክለቦች ወደ ከተማዋ መግባታቸው ታውቋል፡፡ የውድድሩ የምድብ ድልድል ነገ በድሬዳዋ ስፖርት ኮሚሽን አዳራሽ የሚካሄድ ሲሆን አርብ ውድድሩ በይፋ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

______________________________________________________

ከሲዳማ ቡና ይለቃል ተብሎ ሲነገር የነበረው እንዳለ ከበደ በክለቡ ለ2 አመት የሚቆየውን አዲስ ውል መፈራረሙ ተወርቷል፡፡ እንደ ስፖርት ፋና ዘገባ ከሆነ የመስመር አማካዩ በሁለት አመት ውስጥ 1.3 ሚልዮን ብር ያገኛል ተብሏል፡፡

_________________________________________

ስማቸው ከተለያዩ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ጋር እየተያያዘ የሚገኘው የሱሉልታ ከነማው አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው አሁን ሙሉ ትኩረታቸው በብሄራዊ ለጉ ውድድር ላይ መሆኑን ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ ሙሉ ትኩረት ማድረግ የምፈልገው ቡድኔን ወደ ፕሪሚር ሊጉ ማሳደግ ላይ ነው፡፡ ወደፊት የሚፈጠረውን አብረን የምናየው ይሆናል›› ብለዋል፡፡

______________________________________

በዝውውር መስኮቱ አንድ ተጫዋች ብቻ ያስፈረመው ኢትዮጵያ ቡና ትኩረቱን ወደ ብሄራዊ ሊጉ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ ክለቡ በውሰት የሰጣቸውን ተጫዋቾች ብቃት ለመመልከት ወደ ድሬዳዋ እንደሚጓዝም ታውቋል፡፡

______________________________________

በረከት ይስሃቅ ከደደበት ወደ ሀዋሳ ከነማ መዘዋወሩ ይታወሳል፡፡ ሀዋሳ ከነማም ለተጫዋቹ አገልግሎት 1.5 ሚልዮን ብር የሚወጣ ይሆናል፡፡ ከክቡ ባገኘነው መረጃ መሰረት ሀዋሳ ለደደቢት 700ሺህ ብር የሚከፍል ሲሆን ለበረከት የ2 አመት ደሞዝ ደግሞ 800ሺህ ብር በአጠቃላይ 1.5 ሚልዮን ብር ወጪ ያደርጋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *