​ዝውውር | ወልዋሎ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋናዊው የአጥቂ መስመር ተጫዋች ሪችሞንድ አዶንጎን አስፈረመ።

በፕሪምየር ሊጉ የመጀመርያ ተሳትፎው መልካም አጀማመር ካሳየ በኋላ የተቀዛቀዘው ወልዋሎ በአማራጭ እጥረት የተቸገረው የአጥቂ ክፍሉን ለማጠናከር የዛምቢያ ፕሪምየር ሊግ ክለብ በሆነው ቢዩልድኮን ኤፍሲ ቆይታ ያደረገው አዶንጎን ማስፈረም ችሏል።

የ25 አመቱ ሪችሞንድ ሮጀር አዶንጎ በሀገሩ ክለቦች ሊበርቲ ፕሮፌሽናል፣ አሚደስ ፕሮፌሽናል፣ በረኩም ቼልሲ ፣ በኦማኑ ሳሀም ክለብ እንዲሁም በጋና ከ20 አመተረ በታች ብሔራዊ ቡድን ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን ያለፈውን የውድድር አመት በዛምቢያው ቢዩልድኮን ተጫውቷል።

ወልዋሎ በስበስቡ ሁለት የውጪ ዜጎችን (ፕሪንስ ሰቨሪንሆ, ቡርኪናፋሶ እና አብራህማን ፉሴይኒ, ጋና) የያዘ ሲሆን ሶስተኛው የውጪ ተጫዋቹ አዶንጎን ከሁለተኛው ዙር ጀምሮ የሚጠቀምበት ይሆናል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *