​ከ20 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ተጀመረ

ለሁለተኛ ጊዜ የሚደረገው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ2010 የውድድር ዘመን በሁለት ምድቦች ተከፍሎ ይደረጋል። በዛሬው እለትም የመክፈቻ ጨዋታዎች በአሰላ እና ሶዶ ተካሂደዋል።

ከምድብ ሀ አሰላ ላይ በተደረገ ጨዋታ ለመጀመርያ ጊዜ በውድድሩ ላይ የተሳተፈው ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ሌላው የውድድሩ አዲስ ቡድን የሆነው ጭላሎ ፉድ ኮምፕሌክስን አስተናግዶ 1-0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ከምድብ ለ ሶዶ ላይ ከ17 አመት በታች ጨዋታ ቀጥሎ 10:00 ላይ በተካሄደ የአምናው የውድድሩ ቻምፒዮን ሀዋሳ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ 1-1 ተለያይተዋል። ሀዋሳዎች በ16ኛው ደቂቃ ጌትነት አየለ ባስቆጠራት ጎል መሪ መሆን ቢችሉም ወላይታ ድቻዎች በሁለተኛው አጋማሽ ክብሩ በለጠ ባስቆጠረው ጎል አቻ ተለያይተዋል።

ምድብ ሀ

ዕሁድ ጥር 13 ቀን 2010

ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ (ኦሜድላ ሜዳ)

ኢ/ወ/ስ አካዳሚ ከ መከላከያ (አካዳሚ ሜዳ)

ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን (ድሬዳዋ)

ምድብ ለ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሲዳማ ቡና (24 ሜዳ)

አዲስ አበባ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ (ኤሌክትሪክ ሜዳ)

አራፊ – ደደቢት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *