ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ | ዛማሌክ የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ አመሻሽ ላይ ሰርቷል

በካፍ ቶታል ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ወላይታ ድቻን የሚገጥመው የግብፁ ዛማሌክ ዛሬ 10 ሰአት ላይ የነገውን ጨዋታ በሚያደርግበት ሀዋሳ አለምአቀፍ ስታድየም አከናውኗል።

የግብፁ ኃያል ክለብ እሁድ ለሊት ወደ አዲስ አበባ ገብቶ ትላንት ማለዳ የክለቡ አባላት ፣ አመራሮች ፣ ጋዜጠኞች እና በኢትዮጵያ የግብፅ ኢምባሲ ተወካዮችን ጨምሮ 65 የልዑካን ቡድን በመያዝ ሀዋሳ ሮሪ ሆቴል ከትመዋል። ቡድኑ ትላንት የመጀመሪያ ልምምዱን በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ ላይ የሰራ ሲሆን ዛሬ ደግሞ 10 ሰአት ላይ ሁለተኛ እና የመጨረሻ ልምምዳቸውን ጨዋታውን በሚያደርጉበት የሀዋሳ አለምአቀፍ ስታድየም አከናውነዋል፡፡

ለሁለተኛ ጊዜ በተጋጣሚነት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ኢሀብ ጋላል ለጋዜጠኞች ቃለምልልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆኑም በተለያዩ አጋጣሚዎች በሰጧቸው አስተያየቶች አሸንፎ ለመመለስ እንደሚጥሩ እና ስለተጋጣሚያቸው ወላይታ ድቻ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

በተያያዘ የነገውን ጨዋታ የሚመሩት ማሊያዊያን ዳኞች በሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም ልምምዳቸውን ሰርተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *