ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ | ወላይታ ድቻ ነገ ረፋድ ወደ ዳሬሰላም ያቀናል

በኮንፌድሬሽን ዋንጫው ሁለት ወደ ምድብ ድልድል ለማለፍ የመጨረሻ ሁለት ዘጠና ደቂቃ የቀረው ወላይታ ድቻ ከያንግ አፍሪካንስ ጋር ለሚያደርገው የመጀመርያ ጨዋታ ወደ ታንዛኒያ ዳሬሰላም ከረፋዱ 3፡00 ሰአት ላይ ያቀናል ፡፡

ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ የገባው ክለቡ ወደ ስፍራው የሚያመራው 35 የሚደርስ የልዑካን ቡድን ይዞ ሲሆን 18ቱ ተጫዋቾች ናቸው። በቀደሙት ዙሮች ወሳኝ የነበሩት አምበሉ ተክሉ ታፈሰ እና እሸቱ መና በሁለት ቢጫ ካርድ ምክንያት ከክለቡ ጋር ያልተጓዙ ሲሆን አጥቂው ዳግም በቀለም በጉዳት አያቀናም ሲሉ አሰልጣኝ ዘነበ ፍሰህ በተለይ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

አሰልጣኝ ዘነበ ፍስሀ ስለዝግጅታቸው ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጡት አስተያየት “ዝግጅታችን እጅግ ጥሩ ነው። የተጋጣሚያችንን ያንግ አፍሪካንስ ቪዲዮን አግኘተን በሱ ላይ የተመረኮዘ ልምምድን ስንሰራ ነበር። ከሞላ ጎደል በቂ ነገር ይዘናል ብዬ አስባለው። በሊጉ ከመከላከያ ስንጫወት የድካም ስሜት ታይቶብናል። ከዛ ተላቀን ውጤት ይዞ ለመምጣት በሚገባ ተዘጋጅተናል” ብለዋል።

ወደ ዳሬሰላም የሚጓዙ 18 ተጫዋቾች


ግብ ጠባቂዎች

ወንደሰን ገረመው ፣ መሳይ ቦጋለ

ተከላካዮች

ሙባረክ ሽኩር ፣ ውብሸት አለማየሁ ፣ ውብሸት ክፍሌ ፣ ሲሳይ ማሞ ፣ ተስፉ ኤልያስ ፣ ቸርነት ጉግሳ
አማካዮች
ያሬድ ዳዊት ፣ ዘላለም እያሱ ፣ ኃይማኖት ወርቁ ፣ በዛብህ መለዮ ፣ አምረላህ ደልታታ ፣ ታደለ ዳልጋ ፣ እዮብ አለማየሁ

አጥቂዎች

ተመስገን ዱባ ፣ አብዱልሰመድ አሊ ፣ ጃኮ አራፋት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *