አጫጭር የክረምት ወሬዎች

በክረምቱ የሀገር ቤት የተጫዋቾች ዝውውር እና የቡድን ግንባታ ሩጫዎች ቀጥለዋል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም ወሬዎቹን እንዲህ አሰናድታዋለች፡፡

አዳማ የአምሃ በለጠን ኮንትራት ለማራዘም እየተንቀሳቀሰ ነው

አዳማ ከነማ ወደ ፕሪሚየር ሊግ እንዲመለስ ወሳኝ አስተዋፅኦ ካበረከቱ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው አምሃ በለጠን ለማቆየት ጥረቱን ጀምሯል፡፡ የቀድሞው የሀረር ሲቲ ተጫዋች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጥብቅ የሚፈለግ ሲሆን አዳማ ከነማ አምሃን ለማቆየት ቢያንስ እስከ 850,000 ብር ሊያወጣ ይችላል ተብሏል፡፡፡፡

መከላከያ በውል ማራዘም ተጠምዷል

10 የሚሆኑ የመከላከያ ተጫዋቾች ከክለቡ ጋር ያላቸውን ውል ለማራዘም ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ጦሩ ለውል ማራዘሚያው ለእያንዳንዱ ተጫዋች በአማካይ እስከ 750,000 ብር ሊከፍል ይችላል፡፡ መከላከያ ወሳኝ አጥቂው ማናዬ ፋንቱ ወደ መብራት ኃይል አምርቶበታል፡፡

ቡና በፋሲካ ምትክ ላይ አነጣጥሯል

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በቅርቡ በተለያየው ፋሲካ አስፋው ምትክ ሁነኛ አማካይ እያፈላለገ ነው፡፡ ቡና የዳሽን ቢራውን ደረጄ ሀይሌ እና የመከላከያው ጥላሁን ወልዴን ሊያስፈርም ይችላል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ከሁለቱ አማካዮች በተጨማሪ የኢትዮጵያ መድህኑ ብሩክ ጌታቸው እና የዳሽን ቢራውን ሳሙኤል አለባቸው (ግቻው) ለማስፈረም ጥረት ጀምሯል፡፡

ሀዋሳ ከነማ ወሳኝ ተጫዋቾቹን አሰናብቷል

ሀዋሳ ከነማ ግብ ጠባቂው ቢንያም ሀብታሙን አና አጥቂውን አንዱአለም ንጉሴን ማሰናበቱን ታውቋል፡፡ ቢንያም ሀብታሙ ቀጣዩ ማረፊያው ዳሽን ቢራ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዳሽን ጋር ድርድር መጀመሩም እየተነገረ ይገኛል፡፡

ግሩም ስዩም ወደ ዳሽን

አንጋፋው ተከላካይ ግሩም ስዩም ዳሽን ቢራን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል፡፡ ዳሽን ቢራ የቀድሞ የሀረር ሲቲ አስልጣኝ የነበረውን ሳምሶን አየለን 300,000 ብር የፊርማ ክፍያ አሰልጣኙ አድርጎ መሾሙንም አረጋግጧል፡፡

ሳኑሚ እና ዊልያም በቅዱስ ጊዮርጊስ እቅድ ውስጥ አልነበሩም

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰሞኑን የለቀቁትን ናይጄሪያውን ሳሙኤል ሳኑሚ እና ካሜሮናዊውን ዊሊያም ኤሳንጆ በክለቡ የቀጣይ አመት እቅድ ላይ የሌሉ ስለሆኑ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ ሳኑሚ ለደደቢት እንዲሁም ዊሊያም ለመብራት ሀይል መፈረማቸው የሚታወስ ነው፡፡

አል ሂላል የዝግጅት ጨዋታ እያደረገ ነው

ከፊቱ ላሉበት የአፍርካ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች አዲስ አበባ እየተዘጋጀ የሚገኝው የሱዳኑ አል ሂላል አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክለቦች የተወጣጡ ተጫዋቾች ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 31 በሆነ ውጤት አሸንፎል፡፡ በኢትዮጵያው በኩል አይናለም ሀይለ ፣ ቢንያም አሰፋ ፣ ሳሙኤል አለባቸው ፣ መስፍን ኪዳኔ ተሰልፈው ተጫውተዋል፡፡


===== >> ምንጭ — ፕላኔት ስፓርት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *