‹‹ የትኛውንም ጫና ለመቋቋም ዝግጁ ነኝ ›› ኤልያስ ማሞ

ባለፈው ሰኞ ለኢትዮጵያ ቡና በይፋ የፈረመው ኤልያስ ከዝውውሩ በኋላ ለአደገኞቹ በመፈረሙ ኩራት እንደሚሰማው ተናግሯል፡፡

‹‹ክለቡ ለእኔ ያደረገልኝ አቀባበል አስደስቶኛል፡፡ ከዚህ በፊት ለንግድ ባንክ ስፈርም ይህ አይነት ነገር አልነበረም ፡፡ በዚህም ለክለቡ ለመፈረም ያሳለፍኩት ውሳኔ አርክቶኛል፡፡ ›› ብሏል፡፡

ኤልያስ ሌሎች ተቻዋቾች ኢትዮጵያ ቡና ሲገቡ የሚሰማቸው ጫና እንደማይሰማውም ይናገራል፡፡ ‹‹ ከፍተኛ ጫና እንደሚኖርብኝ አውቄው ነው ለኢትዮጵያ ቡና የፈረምኩት፡፡ የትኛውንም ጫና ለመቋቋም ዝግጁ ነኝ፡፡ ›› ኤልያስ በተጨማሪም ንግድ ባንክ ያቀረበለትን የውል ማራዘም ጥያቄ ያልተቀበለበትን ምክንያት ተናገሯል፡፡

‹‹ በክለቡ አሰልጣኝ እና አመራሮቹ አልተፈለግኩም፡፡ በተጨማሪም ክለቡ ለውል ማራዘምያው ያቀረበልኝ ገንዘብ ኢትዮጵያ ቡና ካቀረበው ጋር የሚመጣጠን አይደለም ››

ኤልያስ ማሞ የፈረመበት የገንዘብ መጠን በይፋ ባይገለጥም ተጫዋቹ ከኢትዮጵያ ቡና የ2 አመት 800ሺህ ብር እንደተከፈለው ተወርቷል፡፡

ምንጭ – ዛሚ ስፖርት ብሄራዊ (ሬድዮ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *