በረከት አዲሱ በአዳማ ከነማ ይቆያል

የአዳማ ከነማው የግብ አዳኝ በረከት አዲሱ ስሙ ከበርካታ ክለቦች ጋር ቢያያዝም በክለቡ ለመቆየት እንደሚፈልግ ተወርቷል፡፡

ተጫዋቹ ዘንድሮ ከአዳማ ከነማ ጋር ድንቅ የውድድር ዘመን ያሳለፈ ሲሆን በኢትዮጵያ ቡና እና በደደቢት በጥብቅ ይፈለጋል፡፡ ተጫዋቹም ስለ ዝውውር ጭምጭምታዎቹ የሚሰማውን ተናግሯል፡፡

‹‹ አንዳንድ ክለቦች አናግረውኛል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ብመዘዋወርም ፍለጎቴ ነው፡፡ ነገር ግን ለአዳማ ከነማ ለተጨማሪ አመታት የሚያቆየኝን ኮንትራት መፈረምን ቅድሚያ የምሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ ›› ሲል የእግርኳስ ህይወቱ ነፍስ የዘራበትን ክለብ እንደሚያስቀድም ተናግሯል፡፡

አዳማ ከነማ የወሳኝ ተጫዋቾቹን ኮንትራት ለማራዘም እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡

ምንጭ – ዛሚ ስፖርት ብሄራዊ (ሬድዮ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *