ሳምሶን አየለ ለዳሽን ቢራ አሰልጣኝነት ጫፍ ደርሷል

ባለፈው ሳምንት ዳሽን ቢራ እና አሰልጣኝ ታረቀኝ አሰፋ ስምምነት ላይ ቢደርሱም ሀዋሳ ከነማ በመሃል ጣልቃ ገብቶ ቅሬታ በማሰማቱ የታረቀኝ የዳሽን ጉዞ መስተጓጎሉ ይታወሳል፡፡ አሁን በክለቡ ቀሪ ኮንትራት ያለው ታረቀኝ አሰፋ በሀዋሳ ከነማ የመቆየቱ ጉዳይ እርግጥ እየሆነ መጥቷል፡፡

ዳሽን ቢራ የታረቀኝን መቅረት ተከትሎ የቀድሞው የሐረር ሲቲ አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን በዋና አሰልጣኝነት ለመሾም ለስምምነት መድረሳቸውን ዛሚ ስፖርት ብሄራዊ ዘግቧል፡፡

ሳምሶን አየለ ዳሽን ቢራን ለ2 አመታት ለማሰልጠን የተስማሙ ሲሆን ያለቀውን የውድድር ዘመን በዋና አሰልጣኝነት የጨረሱት ካሊድ መሃመድ የሳምሶን ረዳት ሆነው ይቀጥላሉ፡፡

የቀድሞው የእርሻ ሰብል ተጫዋች ሳምሰሶን አየለ በ2004 ክረምት ሐረር ሲቲን ለረጅም ጊዜ ያሰለጠኑት አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም ወደ ኢትዮጵያ ቡና ማምራታቸውን ተከትሎ በክለቡ ዋና አሰልጣኝነት የተሸሙ ሲሆን በ2006 አጋማሽ በጤና ችግር ምክንያት ስራቸውን እስከለቀቁበት ጊዜ ድረስ የምስራቁን ክለብ በዋና አሰልጣኝነት መርተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *