ኢትዮጵያ ቡና የዳሽን ቢራው የተከላካይ አማካይ ደረጀ ኃይሉን ማስፈረሙን አስታውቋል፡፡ ደረጄ ለኢትዮጵያ ቡና የፈረመው ለ2 አመት ኮንትራት ሲሆን የተዛወረበት የገንዘብ መጠን በክለቡ ይፋ አልተደረገም፡፡
ደረጄ በ2005 ክረምት ዳሽን ቢራ ወደ ፕሪሚየር ሊግ መቀላቀሉን ተከትሎ ካስፈረማቸው በርካታ ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን በጎንደሩ ክለብ አንድ አመት ቀሪ ኮንትራት ነበረው፡፡ ተጫዋቹ እና ክለቡ በደረሱበት ስምምነት ደረጄ የዳሽን ቢራ ቀሪ አንድ አመት ኮንትራቱን ገንዘብ መልሶ ለኢትዮጵ ቡና ፈርሟል፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ ለበርካታ አመታት የመጫወት ልምድ ያለው ደረጄ አመዛኙን የእግርኳስ ህይወቱን ያሳለፈው በሀዋሳ ከነማ ነው፡፡ በ2004 ሀዋሳ ከነማን ለቆ ለአዳማ ከነማ የፈረመ ሲሆን በ2006 ለአንድ የውድድር ዘመን ለዳሽን ቢራ ተጫውቷል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ሶስት አማካዮችን በክረምቱ ካጣ በኋላ በምትኩ ሶስት የአማካይ ተጫዋቾች ግዢ ፈፅሟል፡፡ ደረጄም ኤልያስ ማሞ እና ሚካኤል በየነን ተከትሎ 3ኛው ለኢትዮጵያ ቡና የፈረመ ተጫዋች ሆኗል፡፡
ፎቶ – ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ፌስቡክ ገፅ