ፌዴሬሽኑ በተሰረዙት ጨዋታዎች ዙርያ ውሳኔ አሳለፈ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ሊደረጉ የነበሩና በፀጥታ ጉዳዮች ምክንያት የተሰረዙት ሁለት ጨዋታዎች የሚካሄዱበት ሁኔታ ላይ ፌዴሬሽኑ ውሳኔ አሳልፏል።

ቦዲቲ እና ሀዋሳ ላይ ሊካሄዱ የነበሩት ጨዋታዎች በደቡብ ክልል ካለው ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ አንፃር በክልሉ ተካሂዶ ለሚፈጠረው ችግር ኃላፊነት እንደማይወስድ የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን ማሳወቁን ተከትሎ መርሐ ግብሮቹ ከሚደረጉበት ሜዳ በተለዋጭ አዳማ እና አአ ስታድየም እንዲካሄዱ ተወስኗል።

ሁለቱም ጨዋታዎች ረቡዕ ሰኔ 20 ቀን 2010 የሚከናወኑ ይሆናል

09:00 ወላይታ ድቻ ከ ወልዋሎ (አአ ስታድየም)

09:00 ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና (አዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም)