ቢጫዎቹ በወሩ መጨረሻ በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ላለባቸው የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ሁለት ተጨማሪ ተጫዋቾች በማስፈረም ስብስባቸውን ማጠናከር ቀጥለዋል

በክረምቱ የዝውውር መስኮት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ የሚገኙት እና ቀደም ብለው በባህርዳር ከተማ የአንድ ዓመት ቆይታ ያደረገውን ጋናዊው ሰቲህ ኦሴን ያስፈረሙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮ ኤሌክትሪክ ቆይታ የነበረውን በፍቃዱ አስረሳኸኝ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
ከዓመታት በፊት ሀምበሪቾ ዱራሜን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ካሳደጉ ወሳኝ ተጫዋቾች የነበረው አማካዩ ያለፉትን ሁለት ዓመታትም በኢትዮ ኤሌክትሪክ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ የቻለ ሲሆን አሁን ደግሞ በካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ ወደ የሚሳተፉት የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊዎቹ ወልዋሎዎች ለማምራት ከስምምነት ደርሷል። ሁለተኛው ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ መንጌ ቤንሻንጉል ቆይታ የነበረው የግራ መስመር ተከላካዩ ዑስማን መሐመድ ሆኗል።

