የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ መታሰብያ ውድድር ዛሬ ተጠናቀቀ

በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አዘጋጅነት የሚካሄደው የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ መታሰብያ አመታዊ የታዳጊዎች ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ ዘንድሮ ለ10ኛ ጊዜ የተካሄደው ውድድር በመንግስቱ ልጆች አሸናፊነት ዛሬ ረፋድ ተገባዷል፡፡

በመጀመርያ ለደረጃ በተካሄደው ጨዋታ የአሰላ ልጆች አቢሲንያን 2-1 በማሸነፍ 3ኛ ደረጃ ማግኘታቸውን ሲያረጋግጡ ቀጥሎ በተካሄደው የፍፃሜ ጨዋታ የመንግስቱ ልጆች አፍሮ ፅዮን ኮንስትራክሽንን 1-0 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል፡፡

ከፍተኛ ውጥረት በነበረው ጨዋታ ከፍተኛ የመሸናነፍ ፉክክር የታየ ሲሆን የመንግስቱ ልጆችን የድል ግብ ዮሴፍ ታደሰ በ25ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል፡፡

henok
የውድድሩ ኮከብ ኄኖክ ገ/ህይወት

 

ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ ለውድድሩ ኮከቦች እና አሸናፊዎች ሽልማት የተበረከተ ሲሆን የመንግስቱ ልጆች አሰልጣኝ መንግስቱ አበበ በኮከብ አሰልጣኝነት ተመርጠዋል፡፡ በኮከብ ተጫዋችነት ደግሞ የአሰላ ልጆች አማካይ ኄኖክ ገብረህይወት ተመርጧል፡፡ ኄኖክ ወደፊት ድንቅ አማካይ እንደሚሆን ተስፋ የሚሰጥ እንቅስቃሴ ሲያሳይ ተስተውሏል፡፡

ለ10ኛ ጊዜ የተካሄደው ውድድር 100 ተጫዋቾችን ለቅዱስ ጊዮርጊስ የታዳጊዎች አካዳሚ ያስመረጠ ሲሆን እንደከዚህ ቀደሙም በኢትዮጵያ ክለቦች የሚጫወቱ በርካታ ባለተሰጥኦ ተጫዋቾችን ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የውድድሩ ኮከብ አሰልጣኝ መንግስቱ አበበ
የውድድሩ ኮከብ አሰልጣኝ መንግስቱ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *