ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ማጠቃለያ ውድድሮች ድልድል ወጥቷል

የኢትዮጵያ ከ17 እና 20 ዓመት በታች የማጠቃለያ ውድድሮች የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ዛሬ በባቱ ከተማ ተከናውኗል። 

የእጣ ድልድሉ እና የመጀመርያ ጨዋታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

ከ20 ዓመት በታች ውድድር

ምድብ ሀ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ መከላከያ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ፣ ደደቢት

ሀሙስ ሐምሌ 5 ቀን 2010

08:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ጥሩነሽ ዲባባ (ባቱ ስታድየም)

10:00 መከላከያ ከ ሀዋሳ ከተማ (ባቱ ስታድየም)

ምድብ ለ: ኢትዮጵያ መድን፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ወላይታ ድቻ፣ አአ ከተማ፣ ድሬዳዋ ከተማ

ሀሙስ ሐምሌ 5 ቀን 2010

08:00 ኢትዮጵያ መድን ከ አአ ከተማ (ሼር ሜዳ)

10:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ወላይታ ድቻ (ሼር ሜዳ)

ከ17 ዓመት በታች ውድድር

ምድብ ሀ፡ ወላይታ ድቻ፣ ወጣቶች አካዳሚ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አፍሮ ፅዮን

አርብ ሐምሌ 6 ቀን 2010

03:00 ወላይታ ድቻ ከ አፍሮ ፅዮን (ባቱ ስታድየም)

05:00 ወጣቶች አካዳሚ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ባቱ ስታድየም)

ምድብ ለ: ማራቶን፣ አዳማ ከተማ፣ መከላከያ፣ ሀዋሳ ከተማ

አርብ ሐምሌ 6 ቀን 2010

03:00 ማራቶን ከ ሀዋሳ ከተማ

05:00 አዳማ ከተማ ከ መከላከያ

በውድድሩ ላይ እንደሚካፈሉ ሲጠበቁ የነበሩት የኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና ከ17 ዓመት በታች ቡድኖች እንደማይካፈሉ በማሳወቃቸው ከምድብ ድልድሉ ተሰርዘዋል።