ድሬ ዳዋ ከተማ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

በክረምቱ የዝውውር መስኮት ጥቂት ተሳትፎ እያደረጉ ከሚገኙ ክለቦች አንዱ የሆነው ድሬ ዳዋ ከተማ ፍሬው ጌታሁንን ማስፈረሙን ክለቡ አስታውቋል። 

ክለቡ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ሳምሶን አሰፋን በአመዛኝ ጨዋታዎች የተጠቀመው ድሬዳዋ የሳምሶን ተጠባባቂ የነበረው ጀማል ጣሰውን ወደ ፋሲል ከነማ በመሸኘቱ ተተኪ ግብ ጠባቂ ሲፈልግ ቆይቷል። በአዲስ አበባ ከተማ ዓመቱን ያሳለፈው ፍሬው ጌታሁንንም በሁለት ዓመት ኮንትራት ማስፈረሙ ታውቋል።

ፍሬው በ2007 ድሬዳዋ ላይ በተደረገው የብሔራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ላይ ለአርሲ ነጌሌ ባሳየው ብቃት ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ማምራት ቢችልም በሀለለት የውድድር ዓመታት ብዙም የመሰለፍ እድል ሳያገኝ ክለቡን በመልቀቅ ወደ አዲስ አበባ አምርቶ የመጀመርያ ተሰላፊ በመሆን ዓመቱን ማሳለፍ ችሏል።

ዮሀንስ ሳህሌን አሰልጣኝ አድርጎ የቀጠረውና ፍቃዱ ደነቀ ያስፈረመው ድሬዳዋ በቀጣይ የተጨማሪ ተጫዋቾች እንሚያስፈርም ሲገለፅ አራት ተጫዋቾችም ከ20 ዓመት ቡድኑ ማደጋቸው ተነግሯል።