አውስኮድ ሰብስቤ ይባስን አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯል

አሰልጣኝ መኮንን ገብረዮሐንስን ያጣው አማራ ውሃ ስራ የዋና አሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ በማውጣት ቅጥር ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወቃል። በስተመጨረሻም አሰልጣኝ ሰብስቤ ይባስን አሰልጣኝ አድርጎ ቀጥሯል።

አንጋፋው አሰልጣኝ ሰብስቤ ይባስ ባለፈው ዓመት ፌዴራል ፖሊስን ለቀው ወደ ካፋ ቡና ካመሩ በኋላ ቡድኑ 6ኛ ደረጃ ይዞ እንዲያጠናቅቅ የረዱ ሲሆን በቀጣይ የከፍተኛ ሊግ ውድድርም ያላቸውን ልምድ ተጠቅመው አውኮድን ተፎካካሪ እንደሚያደርጉ ለሶከር ኢትዮጽያ ገልፀዋል።

አሰልጣኝ ሰብስቤ በ1994 ብርሃንና ሰላምን ወደ ፕሪምየር ሊግ ማሳደጋቸው የሚታወስ ሲሆን እርሻ ሰብል፣ ብርሀንና ሰላም፣ ኒያላ፣ ወልዲያ፣ ፋሲል ከነማ፣ ፌዴራል ፖሊስ እና ካፋ ቡና ካሰለጠኑባቸው ክለቦች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።