ድሬዳዋ ከተማ አንድ ተጫዋች አሰናበተ

ድሬዳዋ ከተማ በክረምቱ ካስፈረማቸው የውጪ ዜጎች መካከል በአንድም ጨዋታ ላይ ተሳትፎ ያላደረገውን አጥቂ አሰናበተ።

የምስራቅ ኢትዮጵያው ክለብ በውድድር ዓመቱ ከአሰልጣኝ ዮሐንስ ሰሀሌ ጋር በጊዜ ሲለያይ ወጥ ባልሆነ የውጤት ጉዞ ላይ ይገኛል። ዘንድሮ ቡድኑ ውጤታማ ጉዞ እንዲያደርግ በማሰብ አራት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾችን ማስፈረሙም ይታወቃል። ከነዚህም መካከል  የአጥቂ መስመር ስፍራውን ያጠናክራል ተብሎ የታሰበው ጋናዊውን አጥቂ ኤዝክኤል ቲቴ አንዱ ነው። ይህ ጋናዊ አጥቂ ኤዝክኤል ቲቴ እንደታሰበው ሳይሆን በተቃራኒው ከቡድኑ ጋር በአንድ ጨዋታ ላይ የ18 ተጫዋቾች ዝርዝር ውስጥ ከመካተቱ ውጭ በየትኛውም ጨዋታ ላይ ተሳትፎ አገልግሎት አልስጠም። ይህን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ ተጫዋቹን ያሰናበተው ሲሆን ለመሰናበቱ እንደ ምክንያት እየቀረበ ያለውም አቋሙ ከቀን ወደ ቀን ሊሻሻል ባለመቻሉ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

የ26 ዓመቱ የቀድሞው የኦክዋዉ ዩናይትድ አጥቂ ወደ ጋናው ታላቅ ክለብ ኸርትስ ኦፍ ኦክ በ2014 አምርቶ በከባድ ጉዳት ምክንያት ሶስት ጨዋታዎችን ብቻ አድርጎ አድርጎ ነበር የለቀቀው። ተጫዋቹ በሱዳኖቹ አትባራ አላማል እና አል አህሊ ሸንዲ ጥሩ ጊዜያትን በማሳለፍ በክረምቱ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ቢያመራም አንድም ደቂቃ ተሰልፎ ሳይጫወት ክለቡን ተሰናብቷል። 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *