የአሰልጣኞች አስተያየት | ደቡብ ፖሊስ 1-2 መቐለ 70 እንደርታ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 13ኛው ሳምንት ዛሬ በሀዋሳ ደቡብ ፖሊስ በሜዳው በመቐለ 70 እንደርታ ከተረታ በኃላ የሁለቱ ክለቦች አሰልጣኞች ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ አስተያየታቸውን እንዲህ ሰተውናል፡፡

“እንዳሰብነው በመጀመርያው አጋማሽ ግብ ማስቆጠር ችለናል ” ገብረመድህን ኃይሌ መቐለ 70 እንደርታ 

” ጨዋታው ጥሩ ነበር፤ በመጀመሪያው አጋማሽ  ጨዋታውን ለመጨረስ ኃሳብ ነበረን፡፡ እንዳሰብነው ግብ ማስቆጠር ችለናል፡፡ ከእረፍት በኋላ ግን ጫና ፈጥረውብናል፡፡ እኛ ደግሞ ያገኘነውን ለማስጠበቅ በመሞከራችን ጫና ፈጥረውብናል፡፡ እንደ አጠቃላይ ሶስት ነጥብ ስለሚያስፈልገን ያንን አግኝተናል፡፡ ሜዳውም አስቸጋሪ ነበር፤ በጀመርከው እንቅስቃሴ መቀጠል ይከብዳል፡፡ ”

“ኳሶች በቀላል ስህተቶች ነበር የሚቆጠሩብን “ዘላለም ሽፈራው ደቡብ ፖሊስ

” ጨዋታውን በሁለት መልኩ መመልከት ይቻላል። ከእረፍት በፊት የኛ ቡድን በፍላጎት የተቀዛቀዘበት ነበር። ፍፁም ወርደንም ነበር የታየነው። ይገቡብን የነበሩት ኳሶች በቀላሉ በስህተቶች ነበር፡፡ በዛ ረገድ ወርደን ነበር የታየነው። 

” ከእረፍት በኃላ ይህንን ለማስተካከል ጥረት አድርገናል፤ የተሻለም እንቅስቃሴ ለማድረግ ሞክረን አንድ ግብ ማግባት ችለናል፡፡ ብዙ አማራጮችንም አግኝተን ነበር። ነገር ግን ተቀዛቅዘን ነበር የታየነው። ተጫዋቹም ሆነ ባለሙያው ራሱን ማየት አለበት። እንደ አጠቃላይ በዚህ ሁኔታ የምንጓዝ ከሆነ አደጋ ነው። ራሳችንን ከአሁን በኃላ ማየት ያስፈልገናል፡፡ ወደ ታች ሊወስደን የሚችል ስኳድ የለንም። ምናልባት ከዚህ ቀደም ሊጠቀስ የሚችለው ግብ አናገባም፤ የዛሬውን ጨዋታ ጨምረን ባለፉት ጨዋታዎቻችን ቢያንስ አንድ ግብ እናገባለን፡፡ ማግባት ከቻልን ደግሞ ለምን ይገባብናል፤ በተለይ ደሞ በሜዳህ። ሁሉም አሁን ቡድኑን እያበረታታ ነው። የቀረው  የቤት ስራ እኛ ጋር ነው፡፡ 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *