ኢትዮጵያ ቡና አንድ ተጫዋች አስፈረመ

ኢትዮጵያ ቡና በሁለተኛው የውድድር ዘመን አጋማሽ ራሱን አጠናክሮ ለማቅረብ የዝውውር እንቅስቃሴ በመጀመር ሄኖክ ካሳሁንን በዛሬው ዕለት አስፈርሟል።

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ በዓመቱ መጀመርያ ስሑል ሽረን ተቀላቅሎ በመደበኝነት እየተጫወተ የነበረ ቢሆንም ከክለቡ ጋር በተፈጠረው አለመስማማት ምክንያት ከሳምንታት በፊት ውሉን በስምምነት አቋርጦ መለያየቱ የሚታወስ ነው። አሁን ደግሞ ኢትዮጵያ ቡናን በሁለት ዓመታት ውል መቀላቀሉ ተረጋግጧል።

በደደቢት የእግርኳስ ህይወቱን ጅማሮ ያደረገው ሄኖክ ካሳሁን አዳማ ከተማ፣ ጅማ አባ ቡና፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ስሑል ሽረ የተጫወተባቸው ሌሎች ክለቦች ናቸው።

የመጀመርያው የውድድር ዘመን በተከታታይ ሽንፈቶች የውጤት ቀውስ ውስጥ ሆኖ ያጋመሰው ኢትዮጵያ ቡና ሄኖክን ማስፈረሙ በተከላካይ አማካይ ስፍራ ያለበትን በአማራጭ ችግር ለመቅረፍ ይረዳዋል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *