ጅማ አባጅፋር ከአማካይ ተጫዋቹ ጋር ተለያየ

በክረምቱ የዝውውር መስኮት ኢትዮጵያ ቡናን በመልቀቅ ጅማ አባጅፋርን ከተቀላቀሉ እና የሊጉ ልምድ ካላቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ኤልያስ ማሞ ዛሬ ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ጅማ ጅፋር በሁሉም ውድድሮች ካደረጋቸው 19 ጨዋታዎች በሰባቱ የመጀመርያ ተሰላፊ ሆኖ (ከሁለት ጨዋታ በቀር በሌሎቹ ተቀይሮ ወጥቷል) ሲጫወት እና በአንድ ጨዋታ ተቀይሮ በመግባት አንድ ጎል ያስቆጠረ ሲሆን በተለይ በመጨረሻዎቹ ጨዋታዎች ላይ በተደጋጋሚ ከአሰላለፍ እና ከ18 ተጫዋቾች ዝርዝር ውጪ መደረጉ ከክለቡ ጋር ለመለያየቱ እንደምክንያት ተጠቅሷል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና ኤልያስ ማሞ ከዚህ ቀደም የተጫወተባቸው ክለቦች ናቸው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *