ደቡብ ፖሊስ የመስመር ተጫዋች አስፈረመ

ደቡብ ፖሊስ ከስሑል ሽረ ጋር የተለያየው ኪዳኔ አሰፋን አስፈርሟል፡፡

የመስመር አጥቂው ኪዳኔ አሰፋ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ጅማ አባ ቡናን ለቆ ወደ ሽረ ቢያመራም ከክለቡ ጋር በተፈጠረው አለመስማማት ከሳምንታት በፊት ውሉን በማቋረጥ መለያየቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ አዲስ አዳጊውና በወራጅ ቀጠናው ውስጥ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስን በአንድ ዓመት ውል ተቀላቅሏል።

ከዚህ ቀደም በዲላ ከተማ ከአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ጋር የሰራው ተጫዋቹ ዳግም ከአሰልጣኙ ጋር ለሁለተኛ ጊዜ በደቡብ ፖሊስ ተገናኝቷል።

አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ከመሰናበታቸው በፊት ሁለቱ ናይጄሪያዊ አጥቂዎች ፊሊፕ ዳውዝ እና ላኪ ሰኒን ያመጣው ፖሊስ ፊሊፕ ዳውዝ በፋሲል ቆይታው ቅጣት የነበረበት በመሆኑ እንደማይቀጥል የተነገረ ሲሆን ላኪ ሰኒ ግን በሁለተኛው ዙር በክለቡ የምናየው ሌላኛው ፈራሚ ነው፡፡

ደቡብ ፖሊስ በቀጣይ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማምጣት መዘጋጀቱ ሲሰማ በርከት ካሉ ተጫዋቾች ጋርም ሊለያይ እንደሚችል ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *