የአሰልጣኞች አስተያየት | ጅማ አባ ጅፋር 0-0 ፋሲል ከነማ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አስረኛ ሳምንት ተሰትካካይ መርሐ ግብር ጅማ አባ ጅፋር እና ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን ያለ ጎል ከፈፀሙ በኋላ የሚከተለውን አስተያት ሰጥተዋል።

” ከኛ ይልቅ እነሱ የፈለጉትን ውጤት ያሳኩ ይመስለኛል ” የሱፍ ዓሊ – ጅማ አባ ጅፋር

” የዛሬው ውጤት አይገባንም ነበር። ወደ ጎል በተደጋጋሚ መድረስ የተሻልን ነበርን። ከኛ ይልቅ እነሱ የፈለጉትን ውጤት ያሳኩ ይመስለኛል።

” በጥቂት ቀናት ልዩነት መጫወት ከጀመርን ሁለት ወር ሆነን። አሁን ራሱ 72 ሰዓት ሳይሆነን ነው የተጫወትነው። እንዲያም ሆኖ ጎል አለማስቆጠራችን ነው እንጂ ጥሩ ተጫውተናል።

” በተደጋጋሚ ፋሲልን እንዳየነው ኳስ የሚቆጣጠር ቡድን ነው። ስለዚህ አማካይ ክፍል ላይ ኳስን የሚነጥቁ ተጫዋቾችን ነበር የተጠቀምነው። ከእረፍት በኋላ ጉልበት እየጨረሱ ሲመጡ ኳስ የመቆጣጠር ዝንባሌ ያላቸው ተጫዋቾች አስገብተናል። በተጨማሪም እነ መስዑድ በተደጋጋሚ እየተጫወቱ ድካም ላይ ስለሆኑ ነው ያሳረፍነው።

” በጠበቅነው ደረጃ አልተጫወትንም ” ውበቱ አባተ – ፋሲል ከነማ

” ጨዋታው ጠንካራ ነበር። በሁለቱም በኩል ጥሩ ፉክክር ነበር። እኛ እንደ ቡድን ካለፉት ጊዜያት የደከመ እንቅስቃሴ ነበር ያደረግነው። ከሜዳ ውጪ እንደመጫወታችን መጥፎ ነበርን ማለት ባይቻልም በጠበቅነው ደረጃ እና የጨዋታ ፍጥነት ተጫውተናል ማለት አልችልም። እያረፍን ወደ ጨዋታ እየተመለስን መጫወቱ ጥሩ አይደለም። ተጫዋቾችንም ከሪትም ይወጣሉ ያ ይመስለኛል ዛሬ እንደተጠበቀው እንዳንጫወት ያደረገን። ”


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *