ፋሲል ከነማ የውሰት ጥያቄ ለቅዱስ ጊዮርጊስ አቀረበ

በሁለተኛው አጋማሽ የውድድር ዘመን በአጥቂ መስመር በኩል ያለበትን መሳሳት ለመቅረፍ ፋሲል ከነማ ሁለት ተጫዋቾችን በውሰት እንዲሰጡት ለቅዱስ ጊዮርጊስ እግርኳስ ክለብ በደብዳቤ ጠየቀ።

በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመሩት ዐፄዎቹ በውድድር ዓመቱ አጋማሽ በአስራ አምስት ጨዋታ 25 ነጥቦች በመሰብሰብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው መልካም የሚባል የውድድር ጊዜ እያሳለፉ ይገኛል። ሆኖም በሁለተኛው ዙር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እና በአጥቂ በኩል ያለባቸውን መሳሳት ለመቅረፍ ሁለት የፈረሰኞቹን አጥቂዎች ውሰት ጠይቀዋል። ከተስፋ ቡድን ጅማሮውን አድርጎ ያለፉትን አራት ዓመታት በዋናው ቡድን ማገልገል ላይ የሚገኘውን አቡበከር ሳኒ እና በ2009 መጨረሻ ከጅማ አባቡና ፈረሰኞቹን የተቀላቀለው አሜ መሐመድ ናቸው የተጠየቁት።

ፋሲል ከነማ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ቅዱስ ጊዮርጊስ እስካሁን ምላሽ ያልሰጠ ቢሆንም በቅርቡ የክለቡ የቦርድ አመራር በጉዳዩ ላይ በመነጋገር ምላሽ ሊሰጥ እንደሚችል ሰምተናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *