ፌዴሬሽኑ ለ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በቀጣዩ ወር ለሚሳተፍበት የ”ሠላም እና ወዳጅነት ዋንጫ” ውድድር ዝግጅት የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ ወጥቷል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው መስፈርት መሠረት በ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ ላይ እየሰሩ የሚገኙ አሰልጣኞች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሲሆን ከካፍ የስራ ቋንቋዎች ቢያንስ አንዱን መናገር የሚችል፣ ከ10ኛ ክፍል በላይ የሆነ እና ከቢ ላይሰንስ በላይ ያለው፣ የአስተዳደራዊ እና የስልጠና ዕቅዱን በዝርዝር የሚያቀርብ እና በዜግነት ኢትዮጵያዊ ለውድድር እንደሚቀርብ ተጠቅሷል።

ለብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝነት ፍላጎት የላቸው መመዝገብ የሚችሉት እስከ መጋቢት 5 እንደሆነ ተገልጿል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *