ዋለልኝ ገብሬ እና ወልዋሎ ተለያይተዋል

ባለፈው ዓመት መጀመርያ ወልዋሎን በመቀላቀል ከክለቡ ጋር አንድ ዓመት እና ስድስት ወር ቆይታ ያደረገው የአማካይ ክፍል ተጫዋች ዋለልኝ ገብሬ በትላንትናው ዕለት በራሱ ፍቃድ ክለቡን ለመልቀቅ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

የቀድሞ የኤሌክትሪክ እና የንግድ ባንክ አማካይ ባለፈው ዓመት ወልዋሎ በሊጉ እንዲቆይ ከፍተኛ ድርሻ ከተወጡ ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን በዚ ዓመት በአዲስ አበባ ስቴድየም ከ መከላከያ ጋር በተደረገ ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ለበርካታ ግዜያት ከሜዳ ርቆ ቢቆይም ባለፈው ወር ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ መመለሱ ይታወሳል።

በዚህ ወር ከሶስት ተጫዋቾች ጋር በስምምነት የተለያዩት ቢጫ ለባሾቹ በተቀሩት የዝውውር ቀናት ተጫዋች ያስፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *