ዘላለም በረከት እና ስሑል ሽረ ተለያዩ

ላለፉት አራት የውድድር ዓመታት ከስሑል ሽረ ቆይታ አድርጎ የነበረው ዘላለም በረከት ከቡድኑ ጋር በስምምነት ተለያየ።

በ2008 ቡድኑ ከብሔራዊ ሊግ ካደገበት ዓመት ጀምሮ ላለፉት አራት የውድድር ዓመታት የስሑል ሽረን ተከላካይ መስመር ሲመራ የነበረው ዘላለም በረከት በመጀመርያው ዙር ሽረዎች ባደረጓቸው የሊግ ጨዋታዎች ላይ ከዲሜጥሮስ ወልደሥላሴ ጋር በመጣመር በሁሉም ጨዋታዎች ተሰልፎ ተጫውቶ ነበር።

በሁለተኛው ዙር የዝውውር መስኮት በርካታ ተጫዋቾች በማስፈረም እና ሁለት ተጫዋቾች ወደ ዋናው ቡድን በማሳደግ አዲስ ቡድን ገንብተው ወደ ውድድር የቀረቡት ስሑል ሽረዎች በሁለተኛው ዙር ካደረግዋቸው ሶስት ጨዋታዎች አራት ነጥብ አግኝተው በአስራ አምስተኛ ደረጃ ይገኛሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡