የወልቂጤ ቅጣት በገደብ እንዲቆይ ተወሰነ


በቅርቡ ከፌዴሬሽኑ ከበድ ያለ ቅጣት ተላልፎበት የነበረው ወልቂጤ ከተማ በደብዳቤ ይግባኝ መጠየቁን ተከትሎ አቤቱታው እስኪታይ ድረስ የቅጣቱ ውሳኔ በገደብ ታግዶ እንዲቆይ ፈዴሬሽኑ ወስኗል።

የካ ክፍለ ከተማ ከወልቂጤ ያደረጉት ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ የወልቂጤ ደጋፊዎች ከፀጥታ አካላት ጋር በፈጠሩት ግጭት የዲሲፕሊን ኮሚቴም ጥፋተኛ ነው ባለው የወልቂጤ ከተማ እግርኳስ ክለብ ላይ የ100,000 ብር ቅጣት እና ሦስት የሜዳው ጨዋታዎችን ከከተማው 200 ኪ/ሜ ርቀት እንዲጫወት በቅርቡ መወሰኑ ይታወቃል።

የፌዴሬሽኑ የቅጣት ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት ወልቂጤ በደብዳቤ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን ፌዴሬሽኑሙ የወልቂጤ የይግባኝ አቤቱታ እስኪታይ ድረስ የቅጣቱ ውሳኔ በገደብ ታግዶ እንዲቆይ ወስኗል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡