ስለዩጋንዳ ክሬንስ የሴካፋ ቆይታ
ስለተሰነዘረባቸው ትችት
”በሁሉም ውድድሮች ላይ የማሰለጥናቸው ብድኖች ለተሳታፊነት አይመጡም ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን እንጂ፡፡ በዩጋንዳ የሚገኙ አንዳንድ ሰዎች ይህ ቡድን ደካማ ነው ብለው ነበር፡፡ ሆኖም ግን እኛ ውድድሩን በማሸነፍ አፀፋውን መልሰናል፡፡ እኛ የተቹንን እናከብራለን፡፡ የምናከብረው ደግሞ ጨዋታዎችን በማሸፍ ነው፡፡”
ስለ ኤልያስ ማሞ ኤልያስ ማሞ
”የሴካፋ ዋንጫ ኮከብ ተጫዎች ተብሎ በመመረጡ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከለቀቅኩ በኃላ ኤልያስ በቂ የመጫወት ግዜ ባለማግኘቱ ትንሽ ዕድገቱ ተጓቶ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ጥሩ የሆኑ ፈጣሪ አማካዮች እያጣች ነው፡፡ ከዚህ በፊት ሙሉዓለም ረጋሳ እና አሸናፊ ግርማን የመሳሰሉ ፈጣሪ ተጫዋቾች ነበሩ፡፡ አሁን ግን በሚያሰጋ መልኩ ፈጣሪ ተጫዋቾችን እያጣች ነው፡፡ ኤልያስ በቀጣዩ ግዜ የተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚደርስ ተስፋ አለኝ፡፡”
ስለክሬንስ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ
”የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ምድባችንን እየመራን ነው፡፡ በ2015 ኤኳቶልያል ጊኒ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ከጫፍ ደርሰን ነበር የቀረነው፡፡ አሁን እራሳችንን በደንብ እየመረመርን ነው፡፡ አሁንም ስራዎችን መስራት አለብን፡፡”
ስለኢትዮጵያ የሴካፋ መስተንግዶ
”ኢትዮጵያ ውድድሩን በማዘጋጀቷ ደስተኛ ነው፡፡ ሴካፋ በ2014 አልተካሄደም ነበር አሁን ግን ኢትዮጵያ የአዘጋጅነቱን ሀላፊነት ተቀብላ ጥሩ የሆነ ውድድር ማዘጋጀት ችላለች፡፡ ይህም ኢትየጵያ በ2020 የቻን አዘጋጅ መሆን መቻሏ ተገቢ መሆኑን አይቻለው፡፡ እንደኳፍ መስራች አባልነታችሁ ካፍ በ2025 የአፍሪካ ዋንጫን ማዘጋጀት ዕድል ለኢትዮጵያ መስጠት አለበት ብዬ አስባለው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለነበረን ጥሩ ቆይታ ኔክሰስ ሆቴል እና ኬሮደን ሆቴልን ማመስገን እፈልጋለው፡፡ ”